ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ (በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

ከአንድ ወር በፊት በየካቲት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በብሔራዊ ቴያትር አዳራሽ አንድ መጽሐፍ ተመርቆ ነበር፡፡ የመጽሐፉም ርዕስ “ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ” (2004) ይሰኛል፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊ፣ ገጣሚውና መምህሩ ዮሐንስ አድማሱ (ከ08/01/1929-04/10/1967 ዓ.ም) ሲሆን፣ በ1965 ዓ.ም በዓለማያ እርሻ ኮሌጅ ሳለ እንደጻፈው በመቅድሙ ላይ ገልጾታል (ገጽ-xv):: ከሠላሳ ዘጠኝ አመታት በኋላ፣ የጸሐፊው ሁለተኛ ታናሽ ወንድም፣ ዶ/ር ዮናስ አድማሱ (05/02/1935-01/06/2005 ዓ.ም) አሰናኝቶት በግንቦት 2004 ዓ.ም ወደ ማተሚያ ቤት ገብቷል (ገጽ-x)፡፡ ጸሐፊው ዮሐንስና አሰናኙ ዶ/ር ዮናስ፣ የባለታሪኩን የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴን (ከ23/08/1887-30/10/1939) ድረስ ያለውን የሕይወቱንና የሥራዎቹን ታሪክ በትጋትና በቅንነት ሊያቀርቡ ጥረዋል፡፡ Read more at semnaworeqblog.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.