ሽብሩን ያስተባበረው “ኤልያስ ክፍሌ ነው” አሉ ባለስልጣናቱ!!

ሁለት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት ሰበብ ያሰረው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በአሸባሪነት የተጠረጠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ዘጠኝ ሌሎች ሰዎች ጥቃት ለመፈጸም ይንቀሳቀሱ እንደነበር ገልጸዋል።

የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ጋዜጠኞች በተገኙበት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “በከተማ ውስጥ ሊደረግ የነበረውን ሽብር በማስተባበር፤ እንዲሁም ገንዘብ ለውብሸት ታዬ በመላክ ዋናውን ሚና የተጫወተው የኢትዮጵያን ሪቪው ዋና አዘጋጅ አቶ ኤልያስ ክፍሌ ነበር” በማለት ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።

ይህንን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ አቶ ኤልያስ ክፍሌ ስልክ ደውለን ነበር። አላገኘናቸውም። የሚሰጡት ምላሽ ካለ እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 29, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.