ወያኔ በሻለቃ አድማሱ መላኩ የፈጸማቸው ዘጠኙ ድብቅ ደባዎች

(እውነቱ ተሠማ ከአዲስ አበባ) [PDF]  – ማሳሰብያ ይህ ጽሁፍ ለ EMF የተላከው ከአንድ የ KIC ከፍተኛ አመራር ነው :: – በውል እንደሚታወቀው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ተልዕኮውን ፈጽሞ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስረክቧል፡፡ በመቀጠል ደግሞ በዋናነት በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና በሌሎች ሦሥት ፓርቲዎች የተገነባው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስከረም 14 ቀን 1998 ዓ.ም በውህደት ተመሥርቷል፡፡

በዚህ ታሪካዊ ሂደት ከመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ምሥረታ ወቅት አንስቶ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች ይዘው የተነሱትን ሕዝባዊ ዓላማ ለማክሸፍ በቀበሮ ባህታዊነት ያደፈጡ ቦርቧሪዎች እንደነበሩ ይታወቃል፤ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ሥራቸው አጋልጧቸው በመንገድ ላይ ተተፍተዋል፡፡ የሠሩት ወንጀል አስበርግጓቸው ማንም ሳያባርራቸው የፈረጠጡም ነበሩ፡፡ የተቀሩት ግን ድብቅ አጀንዳቸውን እንደ ያዙ በእውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አድፍጠው እስከ ቅርብ ጊዜ ሊኖሩ ችለዋል፡፡ ከእነዚህ ድብቅ አጀንዳ አራማጆች አንዱ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ናቸው፡፡

ዛሬ ስለ እኚህ ሰው ማንነት አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት የፈለኩት ለረጅም ጊዜ በቅርበት ስለማውቃቸውና በህዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን በደልም አላቆም ስላሉ ሰዎች ማንነታቸውን ተገንዝበው እንዲጠነቀቁአቸው ለማሳሳብ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትበውጭ አገር ተቀምጠው መልካም ምግባር ያላቸው አስመስለው የሚያነበንቡትን የእኚህን ሰውዬ ማንነት ሁሉም እንዲያውቀው ማድረጉ ተገቢም አስፈላጊም ሆኗል፡፡

ድርጅቱ ቦርቧሪነታቸውን ተገንዝቦ እርምጃ ይወስዳል ብዬ ለረጅም ጊዜ ስጠብቅ ከነአካቴው ወደ ውጭ አገር ላካቸው፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ በግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም በተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ተሳትፈዋል፡፡ በሕይወት መናቸው ሁሉ እንደ ምሥጥ ውስጥ ለውስጥ ከመሄድ በስተቀር አንድም ጊዜ በልበ ሙሉነት አንድን ነገር የመጋፈጥ ወኔ ኖሯቸው አያውቅም፡፡ በመሆኑም እኚህ ሰው መፈንቅለ መንግሥቱ እንደ ከሸፈ ይርበተበቱ ገቡ፡፡ በወቅቱ የነበረው መንግሥት ደግሞ የእኚህን ሰው ደካማ ጎን ልብ ብሎ አስተዋለ፡፡ ከዚህ በመነሳት እሳቸውን ከመግደል ወይም ከማሰር ይልቅ በመረጃ ምንጭነት መጠቀምን መረጠ፡፡ እሳቸውም የተጠየቁትን ሁሉ ዘከዘኩ፡፡ በእሳቸው መረጃ ሰጭነት ከበታች ሹማምንት እስከ ጄኔራል መኰንኖች እየተያዙ ታሠሩ፡፡ብዙዎቹም ተረሸኑ፡፡ አንዳንዶች አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ግን ይህ የክህደት ተግባራቸው እንደ ውለታ ተቆጥሮላቸው ወዲያው ተለቀቁ፡፡ ከእስር ቤት ጥለውን ወጡ፡፡ በእሳቸው መረጃ ሰጭነት ከተያዙት ብዙዎች ለዓመታት ታሰሩ፡፡ ጓደኛቸው በመሆኔ ይህን በቅርብ በሚገባ አውቃለሁ፡፡ በክሕደት ተግባራቸው ጓደኞቻቸውን አስቀብረው በሕይወት ቀርተው ሕይወትን አጣጣሙ፡፡ አንድ በሉ!

ስለ እውነት በእውነት እንነጋገር፡፡ ሻለቃ አድማሱ ጥቅም እስካገኙበት ድረስ ለሰው ልጅ ጤነኛ ኅሊና ተቃራኒ የሆኑ ማንኛውንም ዓይነት እኩይ ድርጊቶች ይፈፅማሉ፡፡ ፈጽመዋልም፡፡ ለዚህም ማስረጃዎች አሉኝ፡፡ እስቲ እንመልከት፡፡ ወዳጅም ሆነ ጠላት በውል እንደሚያስታውሰው በዚህች ለዘመናት ታፍራና ተከብራ በኖረች ጥንታዊት አገር ላይ ዘረኞች የጎሣ መርህ ሥርዓተ – አገዛዝ እንደ ዘረጉ ለሺህዎች ዓመታት ተከባብረው የኖሩት የኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች በአማራ ሕዝብ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ ከፍተኛ ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡

በዚህ ምክንያት አንዳንድ የጠላት መሣሪያ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች በንፁሐን የአማራ ልጆች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ችለዋል፡፡ በተጓዳኝም የኢትዮጵያ ሕልውና መቀጠሉ አጠራጣሪ ሆነ፡፡ እንግዲህ በእነኚህ ተጨባጭ ምክንያቶች በክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስና በሌሎች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ተነሳሽነት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ሊመሠረት በቃ፡፡ መዐሕድ እንደተመሠረተ ሻለቃ አድማሱ መላኩ በድርጅቱ ውስጥ በተላላኪነት ተቀጠሩ፡፡ አንድ ከፍተኛ ኰንን ድብቅ አጀንዳ ከሌለው በስተቀር እንዴት በተላላኪነት ሊቀጠር ይችላል? ተላላኪ የመሆናቸው ነገር በወቅቱ ብዙዎቹን አነጋግሯል፡፡ ዓላማቸውን በኋላ ደግሞ በተግባር አሳይተዋል፡፡

የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) እንደተመሠረተ የኢትዮጵያ አንድነትና የዴሞክራሲ ጠላቶች የድርጅቱን ሕልውና ለማጥፋት ከፍተኛ ክትትል ማድረግ ጀመሩ፡፡ መሪውን ክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስንም ይዘው አሠሩ፡፡ አንገላቷቸው፡፡ በቂ ሕክምናም እንዳያገኙ አደረጓቸው፡፡ የሕግ ልዕልና በጠብመንጃ ኃይል በተደፈጠጠበት አገር ፍትሕ ያለ ለማስመሰል ነጋ ጠባ ወደ ፖለቲካ ፍርድ ቤት አመላለሷቸው፡፡ በደረቅ ወንጀል ከታሠሩና በማኅበራዊ ሕይወታቸው ለመልካም ሥነ-ምግባር ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን ከፈፀሙ እስረኞች ጋር ባንድ ቤት ውስጥ በማሠር ሞራላቸውን ጭምር ተፈታተኗቸው፡፡ ጠላት በክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራትና በትግል አጋሮቻቸው ላይ ይህን ሁሉ ግፍ መፈፀሙ ላያስደንቀን ይችላል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የአንድነት ኃይሎች ሁሉ ያፈሩበት ግን በሻለቃ አድማሱ መላኩ ድርጊት ነው፡፡

ሻለቃ አድማሱ መላኩ በሥራ አጋጣሚ በእጃቸው የገቡትን ለጠላት ጠንካራ መረጃ የሚሆኑትን በርካታ የፓርቲውን ሰነዶች ወስደው ለአቃቤ ሕግ ዘረገፉ፡፡ የአማራ ሕዝብ ልጆች በአደባባይ በግፍ በሚገደሉበት በዚያ በጨለማ ወቅት እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ ክሕደት ፈጸሙ፡፡ በጊዜው የፓርቲው አባል ብቻ ሳይሆኑ ለእሳቸውና ለቤተሰባቸው መተዳደሪያ ደመወዝ ጭምር ይከፈላቸው እንደነበር ሳስታውስ ደግሞ ግለሰቡ የእናት ጡት ነካሽ መሆናቸውም ጎልቶ ይታየኛል፡፡ እንግዲህ ልብ በሉ! ሻለቃ አድማሱ መላኩ ክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራትንና የትግል አጋሮቻቸውን ለማሰቀል የሰነድ ማስረጃዎችን ለጠላት ያቀበሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ ሁለት በሉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በውል እንደሚያስታውሰው የዛሬዎቹ ገዥዎች ሥልጣን ላይ ከወጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ምርጫ ኢ ዴሞክራሲያዊ ነበር፡፡ በሁሉም መልኩ የምርጫን ሕግ የሚቃረን እንደ ነበር አይረሣም፡፡ በዚህ ምክንያት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ምርጫውን አቋርጦ መውጣት ግድ ሆነበት፡፡ በሁለተኛው ምርጫ ወቅት ግን የመላው አማራ ሕዘብ ድርጅት (መዐሕድ) ራሱን ከምርጫ ለማግለል አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ በምርጫው ሳይሳተፍ ቢቀር ገዥው ፓርቲ ሰበብ ፈልጎ የድርጅቱን የሕጋዊነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ይሠርዝ ነበርና ነው፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ ሕጋዊነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይለት ብቻ ጥቂት አባላትን ከጽሕፈት ቤቱ በእጩነት አቅርቦ አስመርጧል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ከተመረጡት አንዱ ናቸው፡፡ እሳቸው ግን ያጋጠማቸውን የመመረጥ ዕድል በመጠቀም ለፓርቲው ከመሥራት ይልቅ ለገዥዎች ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ተስተውለዋል፡፡ በመዐሕድ ውስጥ ሠርገው የገቡ የገዥው ፓርቲ ቅጥረኞችን በማስተባበር መዐሕድን ለማነቅ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውንም ወዳጅም ሆነ ጠላት በውል የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሦስት በሉ!

ግለሰቡ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ተልዕኮውን በሚገባ ፈጽሞ ወደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሲቀየር በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመዋል፡፡ የፓርቲው ስም ተቀይሮ በዜጎች መካከል በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ ሁሉም ለአገሩ አቅም በፈቀደ ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክትበት ሁኔታ መፈጠሩ ለያዙት ድብቅ አጀንዳ መንገዱን እንደሚዘጋባቸው አውቀዋልና፡፡ ሆኖም በግልፅ ወጥተው በአፍራሽ አቋማቸው ለመግፋት ወኔ አልነበራቸውም፡፡ ስለሆነም አድፍጠው ፓርቲውን እየቦረቦሩ ጊዜ ለመግፋት ወሰኑ፡፡ አራት በሉ!

ሰውዬው በፓርቲው ውስጥ ባለማቋረጥ ደባ እየፈጸሙ መሆናቸው ቢታወቅም አውቀው እንደሚመከሩ በመገመት ለብዙ ዓመታት በትዕግስት ሲታለፉ ኖረዋል፡፡ ሆኖም አንዴም የታረሙበት ወቅት አልነበረም፡፡ እኚህ ሰው መኢአድ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጥምረት በቅንጅት ስም በተንቀሳቀሰበት ወቅትም አፍራሽ አቋም ከማንፀባረቅ ወደ ኋላ አላሉም፡፡ የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ በተመደቡበት ወቅትም በርካታ ጠንካራ አባላትን አሳስረዋል፡፡ አስገድለዋልም፡፡ እጅ ከፍንጅ ግን አልተያዙም፡፡ የሆነውን ሁሉ ግን ሕዝቡ በሚገባ ያውቀዋል፡፡ ህዝቡ በጊዜው ለማዕከል ሪፖርትም አድርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ የሻለቃው አምስተኛው   እኩይ ድርጊት ነው፡፡

ሻለቃ አድማሱ መላኩ በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ስም ለተወካዮች ምክር ቤት ከተመረጡት ሰዎች አንዱ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ለደሞክራሲ መስፈን አስፈላጊ የሆኑ ስምንት ነጥቦች ካልተሟሉ ፓርላማ ላለመግባት ባንድ ድምፅ ወሰነ:: የገዢው ፓርቲም የቅንጅት አመራሮችን ሲያስር ሻለቃ አድማሱን ግን ሳያስር ተዋቸው፡፡ ነገር ግን እኚህ ግለሰብ ስልክ እየደወሉ ተመራጮች ሁሉ ፓርላማ እንዲገቡ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ለፓርቲው ውሳኔ የማይገዙ ከሃዲ መሆናቸውን በዚህ ድርጊታቸው ራሳቸው በራሳቸው ላይ መስክረዋል፡፡ ስድስት በሉ!

ከሁሉም በላይ የአመራር አባላት አብዛኞቹ ሲታሠሩ ሻለቃ አድማሱ ሳይታሠሩ የቀሩበት ምክንያት ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ ብዙ ታዛቢዎች የገዥው ፓርቲ የውስጥ አርበኛ በመሆናቸው ሳይታሠሩ መቅረታቸውንም ይናገራሉ፡፡ በተለይም ከምርጫው በኋላ ጭልጥ ብለው ለሥርዓተ-አገዛዙ አገልጋይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰባት በሉ!

ሰውዬው ውጭ ሀገር የሄዱት በፓርቲው ገንዘብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እዚያም የሚኖሩት በፓርቲው ገንዘብ ነው፡፡ ታዲያ እንዴት የፖለቲካ ጥገኝነት በቀላሉ ሊያገኙ ቻሉ? ለገዥው ፓርቲ በምሥጢር በሠሩት ውለታ መሆኑን መጠራጠር የለብንም፡፡ እንዴ? ስምንት እንበል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ የፈጸሟቸው እኩይ ድርጊቶች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በጣም በዝርዝር ሳንገባ በእምቁ ለማስቀመጥ መርጬአለሁ፡፡ ለማነሳቸው ጭብጦች ሁሉ በቂ መረጃ አለኝ! ጥያቄ እስቲ ላንሳ፡፡ ከአመራር አባላት አንዳንዶቹን እየጠቆሙ ያስያዟቸው እኚህ መኰንን መሆናቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን? ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለን፤ አቶ አሰፋ ሀብተወልድንና ሻለቃ አርጋው ካብታሙን አስይዘዋል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ ተጠቀሱ እንጅ ሌሎች በርካቶችንም አስይዘው ማሳሰራቸውን ይታወቃል፡፡ ብዙ ሰው ይህን እውነታ ላያውቅ ይችላል፡፡ ግን እውነት ነው፡፡ ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ፡፡ አንዲህ ዓይነት ከሃዲ ግለሰብ ናቸው ሻለቃው፡፡ ዘጠኝ በሉ!

ሻለቃ አድማሱ የቅንጅት አመራር አባላት ከታሠሩ በኋላ ድብቅ አጀንዳቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ በስፋት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ተመራጮችን ለገዥው በሚመች መልኩ አስተዳደሩን እንዲረከቡ ከፍተኛ ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ዛሬ ‹‹የቅንጅት ስምና አርማ ባለቤት እኛ ነን፡፡›› የሚሉት እነ አየለ ጫሚሶ እንዲፈጠሩ ከገዥው ፓርቲ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሠርተዋል፡፡ሻለቃ አድማሱ የቅንጅት አመራር አባላት በእስር ቤት በነበሩበት ወቅትወይዘሮ ሳባ መኰንን የተባሉትን ጠንካራ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ‹‹ኢንጅነር ኃይሉ መኢአድን በአዲስ መልክ አደራጁ! ብለዋል›› በማለት ለማሳሳት ሞክረዋል፡፡ ወይዘሮ ሳባ ግን ይህን አሳሳች መልዕክታቸውን ስላልተቀበሏቸው ለአገዛዙ የፀጥታ አባላት ጠቁመው ለሦስት ወር በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አሳስረዋቸዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ከጎጃምና ጎንደር አዲስ አበባ የመጡ የፓርቲ ተጠሪዎችን በምሥጢር ጠቁመው አስይዘው አስደብድበዋል፡፡

የአመራር አባላቱ እንደታሰሩ እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን እየጠቆሙ ለማስያዝ እንዲመቻቸው ወዲያው ጸጉራቸውን አጎፍረው፣ጺማቸውን አሳድገውና ጥቁር መነጽር አድርገው የቀበሮ ባህታዊ ሥራቸውን ፈጽመዋል፡፡ ከውጭ አገር ከፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ለእስረኞች ቤተሰብ የተላከውን ገንዘብ ከመሰሎቻቸው ጋር ተቀራምተዋል፡፡ ሻለቃው እንዲህ ዓይነት ሰው ናቸው፡፡ ጥቅማቸውን ብቻ ማዕከል አድርገው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ልጅ መሆናቸውን ይናገራሉ፤ ለዚህ ሕዝብ ግን ክብርና ፍቅር አሳይተው አያውቁም፡፡ ይልቁንም የባለቤታቸው ወገን ለሆኑት ለኤርትራ ተወላጆች ትልቅ ከበሬታ ይሰጣሉ፡፡ ለትግራይ ተወላጆች ደግሞ ባሁኑ ወቅት የኪስ መሐረብ ሆነዋል፡፡ ወሎዬ መሆናቸውን ማንም ያውቃል፡፡ እሳቸው ግን በደረሱበት ሁሉ ጎንደሬነታቸውን ያውጃሉ፡፡ እሳቸው ብቻ በሚያውቁት ምክንያት ወሎዬ መሆናቸው ያሳፍራቸዋል፡፡

አሁን ደግሞ በውጭ አገር ይገኛሉ፡፡ ምናልባት በኢትዮጵያዊነታቸው ሳያፍሩ ይቀራሉ? የሻለቃ አድማሱ መላኩ የግል ኑሮ በግልፅ ከሚታወቀው ገቢአቸው በላይ ነው፡፡ ብራዚሊያ ቮልስዋገን ታርጋው 30667 የሆነ መኪና አላቸው፡፡ እንዲሁም የኤርትራ ተወላጅ የሆኑት ባለቤታቸው ፊያት ሌተስት መኪና ያላቸው ሲሆን ባሁኑ ወቅት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ በኃላፊነት እርከን ላይ ይሠራሉ፡፡ ልጃቸው ዳዊት አድማሱ በቅርቡ ባልታወቀ ሁኔታ በአዲስ አበባ ንግድ ባንክ የኃላፊነት ቦታ ሊይዝ ችሏል፡፡ ንፁሕ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከሥራ ያለ ምክንያት ሲባረሩ የእኚህ ሰውዬ ልጅ ግን ያለ ደረጃው የኃላፊነት ቦታ አግኝቷል፡፡ ቀደም ሲል የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት የተሰጣቸውን ቤት እስከ አሁን እንዲመልሱ አልተደረጉም፤ ቤተሰቦቻቸው ይኖሩበታል፡፡ ይህ ሁሉ የተደረገላቸው ንፁሃንን እያሳሰሩ ለእንግልት ስለዳረጉ የደም ዋጋ ክፍያ ይሆን? በአስኮ አካባቢ ግራውንድ ፕላስ ዋን ሕንፃ እየሠሩ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ገንዘቡን ከየት አመጡት? ለእስረኞች ቤተሰብ በተላከው ገንዘብ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ሆነም ቀረ በሥርዓተ አገዛዙ በምሥጢር እስከሰሩ ገንዘብ እንደማይቸግራቸው ግልፅ ነው፡፡

እኚህ አይረቤ ሰው ባሁኑ ወቅት በውጭ አገር እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን አሳስተው የአገዛዙ ሹማምንት የሰጧቸውን የአሽከርነት ሥራ ከግብ ለማድረስ እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል፡፡ በተለይም ሰኔ 14 እና 15 ቀን 2000 ዓ.ም የተካሄደው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁ አንገብግቧቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ፓርቲውን ለማፍረስ የአቅማቸውን ያህል እንደሚፍጨረጨሩ ደርሰንበታል፡፡ እርግጥ ነው የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር እኚህን ከሀዲ ግለሰብ የሚከተላቸው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ጥቂት የዋሆችን ‹‹የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባል ነኝ›› በማለት ለማሳሳት አቅም እንደማያጡ አውቄአለሁ፡፡ ስለዚህ ከበቂ በላይ ስለእኚህ ሰውዬ መረጃ አቅርቤአለሁ፡፡ ማንነታቸውን በውጭ አገር የሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ በሚገባ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ ሰው ናቸው፡፡

ዛሬ ከአገር ቤት ርቀው የሚገኙ ወገኖቻችንን ለማሳሳት የሚሞክሩት ማንነታቸውን እንደማያውቁ በመገመት ነው፡፡ ‹‹ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል›› ይባል የለ? ያም ሆነ ይህ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ እኚህ የቀበሮ ባህታዊ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አበክሬ እመክራለሁ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 3, 2008. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.