ስቴዲየሙ ሞልቶ ህዝብ ተመለሰ

(EMF) 30ኛውን የሰሜን አሜሪካ ስፖርት እና ባህል ዝግጅት አስመልክቶ በሜሪላንድ የሚደረገው ዝግጅት እንደቀጠለ ነው። ትላንት የኢትዮጵያ ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፤ ሆኖም ፌዴሬሽኑ ካሰበው በላይ እጅግ የበዛ ህዝብ ነበር የተገኘው። በጉዳዩ ላይ የሜሪላንድ ፖሊስ ጭምር ያሰበበት እና የተዘጋጀበት ባለመሆኑ፤ የተዘጋጀውም የመግቢያ ቲኬት በሙሉ በማለቁ፤ ከተጠበቀው መጠን በላይ ያለውን ህዝብ ወደ ውስጥ ማስገባት አልተቻለም። በመሆኑም እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመልሰዋል። ማታም የቴዲ አፍሮ እና የመሃሙድ አህመድ ዝግጅት ቲኬት ቀድሞ በማለቁ፤ በርካታ ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል።

Ethiopians on Ethiopian Day - July 5, 2013

Ethiopians on Ethiopian Day – July 5, 2013

ቀሪውን ዘገባ ይዘን እንቀርባለን አብራችሁን ቆዩ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.