ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ (ተመስገን ደሳለኝ)

Journalist Temesgen Desalegn

Journalist Temesgen Desalegn

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ይህ ዘመቻ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፕሬስ ድርጅት በኩል በ“ጥናት” ስም የወጣው ውንጀላ ቅጥያ ሲሆን፣ በቅርቡ ኢቲቪ ሰርቶ እንዳጠናቀቀው የሚነገርለት ዶክመንተሪ ፊልም ደግሞ “ሳልሳዊ” ዘመቻ ሆኖ ለጥቆ የሚቀርብ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
Continue Reading–>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 14, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ (ተመስገን ደሳለኝ)

 1. andnet berhane

  April 14, 2014 at 4:25 PM

  ታላቁ የብእር የወረቀት ታጋይ ኢትዮጵያዊው ብርቅዮ ተመስገን ደሳለኝ ለቆምክበት ዓላማ ጽናትህ በድፍረትና ሕገመንግስታዊ መብትክን ያስከበርክ እውነትን ምርኩዝ ያደረክ የጊዚያችን ጀግና ሞያ ሆኖብህ ሳይሆን የዜጎችህ ስቅይና መከራ ያንተብለህ የተሸከምክ ወደር የሌለህ ታላቅ ባለታሪክ ሰው ነህ::
  ፈጣሪያችን ከለላ እድሜና ጤና ሰጥቶህ ለቆምክለት ፍትህን መብትንና ነጻነትን ለመጎናጸፍ ለዚያ ቀን እንዲያበቃህ የዘወትር ጸሎቴ ነው:
  ተመስገን ሕዝብን ለማንቃት የሚያስችለው ባለፉት የአለም እንቅስቃሴዎች ታላቅ አስተዋጾኦ ያደረጉት አንተንመሳይ ልዝብትና ጥንካሬ የተላበሱ የስነጽሑፍ ባለሙያዎች መብትና ግዴታን ዜግነትን በማብስሰር አስፈላጊውን መስዋእትነት በመክፈል ከገዥዎች ከጫንቃቸው ወርውረው ነጻነትን የተጎናጸፉ ጥቂቶች አይደሉም: ታድያ ቀደምት አባቶቻችን የባእዳን ወራሪ ጦር መክተው ድምበርና ነጻነት ክብርና ማንነትን ጠብቀውው በአጥንትና በድም ገምብተው ያስረከቡን በመልክና በቋንቋ እኛን መስለው በዘርና በጎሳ ለያይተው ድምበር አስደፍረው መሬት ሸንሽነው ሀገር አልባ ለማድረግ በግልጽ ጠላትነታቸውን በግንባር የምናየው ያንተና አንተን መሰል እንድነ እስክንድር: ሪኢዮት:አንዱዓለም:ውብሸት:አቡበከር ድምጻችን ይሰማ ዘሪሁን አበበ ቀስቶ በቀለ ገርባ ሌሎቹም ስለራሳቸው ሳይሆን ለህዝባቸው ለሃገራቸው በመቆም በመከራከር ስራአቱ አቅጣጫውን እንዲያስተካክል አልያ ሕዝብ መብቱን በሰላማዊና ፍትሃዊ መንገድ ስራአቱን ይገረሥአል በማለታቸው እንድ ወንጀላኛ ዛብጥያ ወርደዋል: መከራን ተጎንጭተዋል ቤተሰቦቻቸውን ልስቃይና ለፍዳ ጥለዋል ታድያ የተቀረው ሰው መሆኑንና ነጻነት ጥያ ቄው የራሱን ድርሻ ሳይከፍል በለእሎች ነጻ ለመሆን ከጠበቀ ቅዠት እንጂ ሕልም የለውም ስለዚህ ነጻነትን በነጻ እንድማይገኝ አምኖ ለመስዋእትነት ያለ ጥሪ ያለ ቀስቃሽ መነሳትና ማወጅ ይጠበቅበታል ::
  ሕዝብ ያሸንፋል
  ኢሓዴግ ይገረሰሳል

 2. መሰለ

  April 17, 2014 at 2:01 AM

  ካቲሊባት