ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ክፍል ሶስት (ተመስገን ደሳለኝ)

Journalist Temesgen Desalegn

Journalist Temesgen Desalegn

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም ‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው›› ይለናል፡፡ በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ ራሷ አሜሪካንን ጨምሮ አብዛኛው የአውሮፓ አገራት ከሞላ ጎደል በዜጎች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ማሕበረሰብ መገንባት ከቻሉት ውስጥ ሲመደቡ፤ ብዙሃኑ የአፍሪካ እና የእስያ መንግስታት ደግሞ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል መንፈስ የተቃኘ አገዛዝ አንብረው፣ የትኛውንም ተግዳሮት በጠብ-መንጃ ዓይን መመልከትን ፈቅደዋል፡፡ ከእነዚህኞቹ መካከል የእኛይቷ ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት፡፡ Continue Reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 22, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.