ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ

ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ በማትኮር፤ አደጋውን ለመቀነስ፤ ቅድመ ጥንቃቄ ስለማድረግ፤ ህክምናና ምርምር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በተረጋገጠው መሰረት በአብላጫ በዓለም ላይ ሴቶችን በማጥቃት ላይ ያለው የጡት ካንሰር ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች በበሽታው በየዓመቱ ሲለከፉ ከነዚህም መሃል በሢ የሚቆጠሩት ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ኮመን ፎር ዘ ኪዩር የተባለው የአሜሪካ ድርጅት እንደአስቀመጠው በአሜሪካን የሚገኙ አብላጫዎቹ አፍሮ አሜሪካውያን መሃል ሁለተኛው ገዳይ በሽታ የጡት ካንሰር እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡ በአፍሪካ ስለዚህ ገዳይ በሽታ የታማሚ መጠንና ስለሚያደርሰውም አደጋ አያም ስለሚሰጠው ትኩረትና ህክምና በትክክል እንዲህ ነው ለማለት ዘገባም ሆነ መግለጫ ስለሌለ ብዙ ማለት ያስቸግራል፡፡ በአፍሪካ የበሽታው ሁኔታ ሊታወቅ የሚችለው ታማሚው በበሽታው ተይዞ ለህክምና ወይም ለመመርመር ወደ ጤና ጣቢያ አለያም ህክምና ማእከል ሲሄድ ብቻ ነው፡፡ አብላጫው የሴቶች ቁጥር በሚኖርበት የገጠሩ ክፍል ስለበሽታው ሁኔታ መዝግቦ መያዝና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡ በብዙም የተለመደ ወይም ሁኔታ የተፈጠረለትም አይደለም፡፡

Read Amharic story in PDF Breast Cancer Amharic Translation

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 7, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ

  1. emu

    October 9, 2013 at 2:19 PM

    Arife program