ስለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምን ይላሉ? (ዳዊት ከበደ ወየሳ – ከአትላንታ)

EMF – ሰሞኑን በግብጽ አገር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ በቲቪ መስኮት እናያለን፤ ወሬውንም እንሰማለን። በግብጽ ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ማቃጠል ማለት ትልቅ ሙዚየምን ማቃጠል እንደማለት ነው። አንዳንዶች ግን ይህን እውነት ዘንግተው በሌላ እምነት ተከታዮች ላይ ባላቸው ጥላቻ ብቻ በመነሳት ታሪካቸውን በአሳፋሪ መንገድ በ እሳት በመጻፍ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ታሪክ ከግብጽ ታሪክ ጋር የሚያመሳስለው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውውም ጭምር ሊሆን ይችላል። የቃጠሎው ዜና ከማሳዘን አልፎ፤ ወደፊት በኢትዮጵያ የማይከሰት ስለመሆኑ መቶ በመቶ ህዝቡ የሚተማመንበት ዋስትና የለውም። ይህን ዋስትና በመጠኑም ቢሆን አለማግኘት ደግሞ መጪውን ግዜ በፍርሃት፤ ህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ በጥርጣሬ ቀለበት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል።

በግብጽ የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ

በግብጽ የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ


በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዮዲት ይሁዲት ተነስታ ቤተ ክርስቲያን አቃጥላለች። ግራኝ አህመድ ብዙ ጥፋት ሰርቷል። አጼ ቶሃንስም ነግሰው ብዙ ሙስሊም በግድ አጥምቀዋል። በሃይማኖት ምክንያት እዚህም እዚያም የደም መፋሰስ ተከስቷል። ወዳለንበት ዘመን ስንመጣ ደግሞ፤ በምኒልክ ዘመን እስላም እና ክርስቲያን በአንድ ገበታ መብላት ብቻ ሳይሆን፤ ተጋብቶና ወልዶ አብሮ መኖር ጀምሯል። ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ ሙስሊሙ ገንዘብ ከማዋጣት ጀምሮ የመሰረት ድንጋዩን ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር አብሮ ጥሏል። በክፉም ሆነ በደግ ዘመን “አገር የጋራ ነው፤ ሃይማኖት የግል ነው” የሚለውን የንጉሠ ነገሥቱን ቃል ይዞ ዘመን ተሻግሯል። ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው።
በአገራችንም ቢሆን ከጥቂት አመታት በፊት “አላህ ኩበር” እየተባለ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል፤ የሃይማኖት አባቶች ተገድለዋል። ይህ ደግሞ በቪዲዮ ተቀርጾ አሁንም online የሚታይ እውነት ነው። ሆኖም የትኛውም ሃይማኖት ከህንጻውና ከሰዎች በላይ በመሆኑ፤ ህንሳው ቢቃጠልን ወይም ጥቂት ሰዎች ቢሞቱ፤ ሃይማኖቱ እንደሃይማኖት ተጠናክሮ ይቀጥላል። በመሆኑም መስጊድ ወይም ቤተ ክርስቲያን ቢቃጠል የእምነቱ ተከታዮች አምላካቸውን ማምለካቸው አይቀሬ ነው። በዚህ የማይናወጥ መሰረተ ሃሳብ ላይ መስማማት ከቻልን፤ ማንም የማንንም ህንጻ ለማቃጠል እሳት አይለኩስም። በማቃጠል እና በመገዳደል ቢሆን ኖሮ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለቱም ሃይማኖት አለመስፋፋት ብቻ ሳይሆን፤ የደም መፋሰሱም በሰፊው በተከሰተ ነበር – ይህ ግን አልሆነም። የሃይማኖት ደም መፋሰስ አለመኖሩ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ጨዋነት፤ ብሎም የሃይማኖት መሪዎቹን አስተዋይነት ያሳያል።
coptic 4
አሁን ላይ ሆነን ያለፈውን ታሪክ የምናነሳው፤ ያለፈ ጥፋታችንን እንዳንደግም ነው። ካለፈው ጥፋታችን የምንማረው አንድ ቁም ነገር ቢኖር… ኢትዮጵያ ውስጥ ህንጻን በማቃጠል፤ ማንም የማንንም ሃይማኖት አለማጥፋቱን ነው። ከዚህ መሰረታዊ እውነታ በመነሳት ወደፊት በፍቅር እንጂ፤ በጸብ የማንኖርባትን ኢትዮጵያ፤ በመከባበር መገንባት ይኖርብናል። ከአንድ አመት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚያነሱት ጥያቄም የመብት ጥያቄ መሆኑን አብላጫው ህዝብ ያምንበታል። በእስር ቤት ከሚገኙት የኮሚቴ አባላት መካከል አንደኛው ሲናገር፤ “እኛ እኮ በምርጫውም ጊዜ ኢህአዴግን እንጂ ቅንጅትን አልመረጥንም” ቢልም እንኳን የቅንጅት ደጋፊ የነበሩ ሰዎች አላዘኑበትም፤ “የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ” ስላለም ኢህአዴግ አላዘነለትም – ትላንት ቅንጅቶች እና ጋዜጠኞች የታሰሩበት ቃሊቲ በሩን ከፍቶ ሁሉንም አስተናግዷል። ነገ ማን እንደሚስተናገድበት የሚያውቀው ግን አንድ አምላክ ነው። እናም እንዲህ ጊዜ እና ሁኔታ በሚፈራረቁበት ዘመን ላይ ሆነን፤ ከነልዩነታችንም ቢሆን፤ ቢያንስ ለሰው ልጆች መብት በእኩል መንፈስ ልንቆም ይገባል።
የሃሳብ እና የሃይማኖት ልዩነት ሊኖር ይችላል። ነገር ግን የሰው ልጅ መብት ሲረገጥ “እሰይ ደግ አደረገ!” የሚል ሰይጣናዊ መንፈስ በውስጣችን ሊኖር አይገባም። ለዚህም ነው… ሙስሊም ወገኖች ሲታሰሩ እና ሲደበደቡ ሌላው ክርስቲያን ወገናቸው ድምጹን ደግሞ ደጋግሞ ሲያሰማ የነበረው። አንዳንዴ የክርስቲያኑም ሆነ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ጩኸት የሚሰማ እስከማይመስል ደረጃ ላይ ቢደረስም እንኳን፤ ኢህአዴግ እያደረሰ ያለውን የግፍ ተግባር ሁሉም ወገን እያወገዘው ይገኛል። የሰብአዊ መብት ረገጣን ማውገዝ ደግሞ ከአንድ የሰለጠነ ህዝብ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን ግፍ የምናወግዘው ውለታ ለመቆጣጠር ሳይሆን፤ የሰለጠነ ህሊናችን ስለሚያስገድደን ነው።
ስለግብጽ ክርስቲያኖች በደል እና ለቅሶ ሙስሊሙም ድምጹን ቢያሰማ፤ ነገ እንዲህ ያለው ነገር በአገራችን እንደማይደገም ዋስትና ይሰጣል

ስለግብጽ ክርስቲያኖች በደል እና ለቅሶ ሙስሊሙም ድምጹን ቢያሰማ፤ ነገ እንዲህ ያለው ነገር በአገራችን እንደማይደገም ዋስትና ይሰጣል


ሆኖም አንድ ነገር ያሳስበናል። ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሌላው ወገን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጎን መቆሙን ደግሞ ደጋግሞ አረጋግጧል። ድምጹንም አሰምቷል። ይህ ድምጽ ግን ከጥቂት ሙስሊም ወገኖች በቀር ሌላው ዘንድ ዘልቆ መግባቱ ያጠራጥራል። ይህንን ለማለት ያነሳሳን ደግሞ ከቢላል ሚዲያ ጀምሮ እስከ ድምጻችን ይሰማ ድረስ የሚገኙ አካላት፤ ሌላው ወገን እያደረገ ያለውን ድጋፍ በሚዲያቸው ሲያቀርቡት ወይም በመልካም ምሳሌነት ሲያወድሱት አይታይም። በዚህ ምክንያት የኛ ድምጽ መሰማቱን እንድንጠራጠር ያደርገናል። አንዳንድ ግዜ ፍቅር እና መተሳሰቡ ከአንድ ወገን ብቻ መምጣት የለበትም። ሌላውም ወገን የተሰጠውን ፍቅር እና ድጋፍ ተቀብሎ ዝም ማለት ሳይሆን፤ ቢያንስ “አመሰግናለሁ” ማለት አለበት። ይህ ሲሆን ነው፤ የምንሰጠው ድጋፍ ተቀባይነት ማግኘቱን የምናውቀው። አሁን ግን አንደኛው ወገን ለፍቅር ሲጮህ፤ ሌላኛው ወገን በዝምታ እየተመለከተ ይመስላልና እኛም “ድምጻችን ይሰማ” የሚል ኮሚቴ አቋቁመን፤ ድምጻችን እንዲሰማ ለሙስሊም ወገኖቻችን በየጊዜው መጮህ ሊኖርብን ነው።
አንድ ነገር ልቸምር። ፍቅርም ሆነ መደጋገፍ ከሁለቱም ወገን ሲሆን መልካም ነው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሁኔታ፤ የታሰሩት ኮሚቴዎች ከተፈቱ የትግላቸው መቸረሻ አድርገው የሚወስዱ ሰዎች አሉ። ሆኖም ጥያቄው ከኮሚቴዎቹ መፈታት በላይ መሆን ይኖርበታል። በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ የታሰሩት ኮሚቴዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ፤ የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞቻችን ጭምር መሆናቸውን ልናስታውስ ይገባል። ትላንት እስክንድር ነጋ ሲታሰር ሙስሊሙም ክርስቲያኑም “ሰብአዊ መብት ይከበር! እስንድር ነጋ አሸባሪ አይደለም!” ብሎ ቢነሳ ኖሮ፤ ኢህ አዴግ የልብ ልብ አግኝቶ የሙስሊሙን ኮሚቴ አባላት አያስርም ነበር። ዛሬ ኮሚቴዎቹም እነእስክንድርም አንድ እስር ቤት ናቸው። አሳሪዎቻችንም ተባብረውብናል። እኛ ከዚያ ውጪ ያለን ሰዎች ስለ ሃይማኖታችን ብቻ ሳይሆን፤ አምላክ ስለሰጠን የሰብአዊ መብት ጭምር በጋራ ልንቆም ይገባናል።
ይህም አለ። በዚህ ፎቶ ላይ በግብጽ የሚገኙ ሙስሊሞች እጅ ለ እጅ ተያይዘው ቤተ ክርስቲያን በሌሎች ሙስሊሞች እንዳይቃጠል ሲከላከሉ ይታያል

ይህም አለ። በዚህ ፎቶ ላይ በግብጽ የሚገኙ ሙስሊሞች እጅ ለ እጅ ተያይዘው ቤተ ክርስቲያን በሌሎች ሙስሊሞች እንዳይቃጠል ሲከላከሉ ይታያል


ወደማጠቃለያችን እናምራ። የትላንት ክፉና ደግ ታሪካችን በአንድነት እንድንጸና እንጂ እንድንለያይ አያደርገንም። በአንድነት ሆነን የምንጮኸው ድምጽ ተመሳሳይ ቃና ሊኖረው ይገባል። ለአንድ ወገን ብቻ መጮኻችን በቂ አይደለም። ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም ለነእስክንድር ነጋም መጮህ ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን፤ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ ግፍ እና በደል ሲደርስ ለነሱም መጮህ ያስፈልጋል። በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል እና ክርስቲያኖች ሲገደሉ ዝም ማለት ትክክል አይደለም። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ቃጠሎውን በደስታ ይቀበሉት ወይም በሃዘን ማወቅ የሚቻለው፤ ሙስሊሙን የሚወክሉ ወገኖች ወጥተው መናገር ሲጀምሩ ነው። የቢላል ሚዲያም ሆነ ድምጻችን ይሰማ ወይም ሌሎች የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች፤ እስካሁን ሌላው ኢትዮጵያዊ ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ቢያቀርቡ፤ ነገ የበለጠ ስራ መስራት ይቻላል። ይህ ብቻ አይደለም – ዛሬ ግብጽ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል ሙስሊም ወገኖቻችን ሲያወግዙ ካልሰማናቸው፤ ነገን መፍራት እንጀምራለን። መተሳሰባችን የእውነት ስለመሆኑ፤ የቃላት ጩኸት ብቻ እንዳልሆነ ለማወቅ ብዙዎች ይጓጓሉ። ስለዚህ የሙስሊሙ መሪዎች ድምጻችን ይሰማችሁ – የናንተንም ድምጽ እንስማ – ወቅታዊ መልእክታችን ነው!!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

9 Responses to ስለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምን ይላሉ? (ዳዊት ከበደ ወየሳ – ከአትላንታ)

 1. Nesanet

  August 17, 2013 at 12:54 AM

  Dawit kebede weyesa and dawit kebede aweramba.the same brothers with different mother .

 2. koster

  August 17, 2013 at 4:32 AM

  We should all stand against injustice and fight the home grown fascists in Ethiopia. There is no Problem between the Ethiopian Moslems and Christians and all tricks to create suspecion and disunity only prolongs woyane ethnic fascism. Please say no to woyane ethnic fascism, ethnic cleansing and state terrorism in Ethiopia. The home grown fascists from Tigrai and their hodam collaborators are preparing Ethiopia for genocide and it is up to those in woyane camp to think twice and reverse their deeds. It is not possible to eliminate Amhara or anyother Group and one cannot bring sustainable peace by preaching fear and hate. http://vimeo.com/18242221

 3. Gragn Ahmed

  August 17, 2013 at 6:52 PM

  Muslims do not burn church. Only cadres burn church or masjid. Please journalist do not post something before reading in depth. Behind the scene, many things happen. Most of what you see in Egypt is the deliberate work of army. So is in Ethiopia. People never do this. One note however, Christians should not just wake up now when they see what they see in Egypt but never woke up when Muslims were tortured to death. So, this is time to wake up for all of us. By the way orthodox are not burning Ethiopian Mesjids but pentes. We have to exclude pentes who are dividing muslims from orthodox.

 4. ኦብጼርቬር

  August 17, 2013 at 8:54 PM

  All Ethiopians who oppose EPRDF’s abuse of human rights must of necessity oppose and condemne EPRDF’s suppressive measures against Ethiopian Muslimes.Religigious freedom is part and parcel of human rights issues.I think the struggle of Ethiopian Muslims is a uniting factor that brings together all Ethiopians,irrespective of religious divide since religious freedom is a basic human rights freedom.Christian Ethuiopians are not doing any FAVOUR to Muslims by supporting them.Supporting their cause is fighting repression in all its forms.

 5. Antale

  August 17, 2013 at 11:40 PM

  Thanks Ato Dawit for your honest opinion. It is about to start honest discussion about muslims – their questions, issues, what they believe especially about their neigohobors we christians
  I also worried that Ethiopian Muslims also may do the same thing- burning Our churches. It does not matter how peacful christian and muslims were living in Ethiopia. The new Islamic movement-whabisim and
  others is those who are not muslims are infidel, unbelievers, untrustworthy, and must be converted or killed. So what makes Ethiopian muslims different than the other moslems in Egypt, Nigeria, Iraq,Phillipines, and many other countries…..Finally, we all remember how much muslims were supporting this governement when it was interfering in our church affair, and busy bulding their mosques infront of every church… may be Ethiopian government has learned a lot about them in the process.

 6. Abebe

  August 18, 2013 at 10:38 AM

  Be Mejemry Derja Eygpt Laay Churche enaa Mosqe Yakatelewu Muslimu Weyem Brother hood Ayedelem! Begzza Hezebu deme Eyewagne yalewu Wetaderu (Ke wetaderume Tekeetu)Newu.Merabawuyanochen lemassdeset Be Netuhan Zegochu deem Yessekerwu Al Sis Newu.JUST KIKE weyane, Ken Kelet Muslimun Ke cerstiyanu Lematalate Tegto Eyeseraa Aydel Ende Merjawochen Wede Hezeb Maddress senfelg Metnkeke Yassefelgale Yeweyan Hodam Cader Eskalehon deresse,Reporter,Addis Admas, Awramba Times…..Tgetewu eyeseru newu ye Ethiopian muslim Lekoshasha Poltica metekemeya Lemadereg Shame on them! http://animalnewyork.com/2013/this-is-what-it-looks-like-just-before-the-muslim-brotherhood-jumps-you/ http://www.middleeastmonitor.com/

 7. andnet berhane

  August 19, 2013 at 8:04 PM

  የተደረገውን ተግባር በፍጽም ሊሆንና ሊደርግ የማይገባው በመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእምነት ጥላቻ ሳይሆን የተነሱበት የመብት ጥያቄ በመሆኑ በግብጽ የተፈጸመው ተግባር ግልጽና የኢትዮጵያ እስልምና ተከታይ ዜጎች በግብጽ ያሉት የእስላም ወንድማማች እንቅስቃሴ ተቃራኒ ለመሆኑ በእምነታቸውና መበመሰረት ጥያቂያቸው ታፍኖና በፍረሃት ተሸብቦ የነበረውን ክርስቲያኑን ሕብረተሰብ በማነቃቃት ያደረጉት አስተዋጽኦ ተጠያቂ የሚያደርጋቸው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን የኳተሊክ የጵ
  ፕሮቴስታት በእስላም ሕብረተሰብ የተነሳውን ድምጽችን ይሰማ ምን ይላሉ ብለን ብንጠይቅ የተሻለ በመሆኑ በምነት ቦታዎችን መቃጠል ሁሉም እንደሚቃወም ማወቅ ይኖርብናል ዳዊት ከበደ ወይሳ ለጠየቅከው ጥያቄ መልሱ ይሄ ሲሆን ወገኖቻችንን በማቅረብ የምናይበት የብዙ ዘመን አብሮነትና የከፈሉት መስዋእትነት መዘንጋት አይገባም እነደጃዝማች አኡመር ሰመተርን ለሎቹንም ማስታወስ ይገባናል

 8. Yezeledaw

  August 21, 2013 at 2:43 AM

  You raised a very genuine and timely question Mr.Dawit and i appreciate your constructive advices.The treat and ideology of Islam should get a due attension when we look at our surrounding and the world at large.We may think positive about Ethiopian muslims as differnet and peace loving but they could be influenced by external forces in and arround the muslim world.We would have the chance to know how much peaceful they are if they have been a majority because, i think ,the problem is worse in those countries where Christians are the minority.In my opinion, the bad part of Islam lies in it’s ideology,principle of the book,to eliminate or forcefully convert all non-muslims to Islam and the growing in number of beleivers who stand for this principle-extremism.Ethiopian muslims are not different to escape from this influence and could be the worest as natives of a poor country who could be easily manipulated by extremist Arab financiers.To conclude my comment,Ethiopian Christians should seriously watch every movement of extremism hand in hand with moderate and peace loving muslim brothers.

 9. 'መታገስ ዋጋ አለው

  September 20, 2016 at 9:31 PM

  ፅሁፉን ከላይ እስከታች በፅሞና አነበብኩት ሆኖም ግን ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ሚዛኑን እጅግ የሳተና አንዱ ወገን ሌላውን የበለጠ በጥርጣሬ እንዲያይ የሚቀሰቅስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ለምሳሌ ከላይ የነ ዮዲት ይሁዲትን የነ አህመድ ግራኝን ..ስም ያለምንም የታይፕ ስህተት ፅፈህ እንዴት የአፄ ዮሃንስን ስም ‘አፄ ቶሃንስ’ ብለህ እንደፃፍከው ገርሞኛል ስማቸውንም ነውራቸውንም አቅርበህ በፍቅር እንደመወቃቀስ ለምን የዚህ አይነት ነገር እንዳደረግክ ትዝብቴን ለአንባቢ ትቼ ወደሌላው ነጥብ ልለፍ!

  ከላይ ወንድሞቼ እንደገለፁት ሁሉ ስለ ግብፁ ቤተክርስቲያናት ቃጠሎ በማንና በምን ምክንያት እንደተቃጠለ ማወቁ ብስለት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን በዚህ ተግባር ደስተኛ የሚሆን ሙስሊም አለመኖሩን ከኖረም ደግሞ ኢምንት ያህሉ ለዚያውን ከአለማወቅና የአብሮነትን ጣእም ካለመረዳት የተነሳ ነው ብለህ ከማለፍ ይልቅ ሁሉም ሙስሊም ደስተኛ ይሆናል ከሚል ኣጉል ጥርጣሬ ክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር ለማነካካት መሞከርህ ዳግም እንድናዝንብህና ኣንድንታዘብህ አድርጎናል ለምሳሌ አምና ላይ ዱባይ ሃገር ለገና እለት ህንፃ በሳት ሲጋይ አንዳንድ ክርስትናን የማይወክሉ ክርስቲያኖች ባለማወቅም ይሁን በጥላቻ “እግዚያብሄር በአረብ ሃገር ላይ ደመራዉን ለኮሰው” ብለው ለመሳለቅና በደስታ ስሜትም እኛ የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ለማብሸቅ ሲዳዳቸው ተመልክተን ነበር ነገር ግን አንድም ሙስሊም ልክ አሁን እንደፃፍከው አይነት ፅሁፍ አውጥቶ ህዝበ ክርስቲያኑን አልወቀሰም በጥርጣሬ አይንም ለማየት አልደፈረም ምክንያቱም ጥቂት በጥላቻ የተሞሉ ግለሰቦች እምነትንም ሆነ የብዙሃኑን ህብረተሰብ አመለካከት አይቀክሉም በሚል ንቆ አልፏቸዋል ለማንኛቅም ነገርን ነገር እያነሳው ታሪክን የኋሊት እያነቆሩ ህዝብን ከህዝብ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ካቶሊኩን ከፕሮቴስታንት ብሄርን ከብሄር ደም ለማቃባት ቂምና ቁርሾን ለመጫር የሚደረጉ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችና ይህን መሰል ፅሁፎች አጥብቀን ልናወግዝ ይገባናል ያዘኑ መስለው የሚያናክሱ ብዙ ናቸውና ጠንቀቅ ማለቱ አይከፋም! ድምፃችን ይሰማም ሃይማኖታዊ ጥያቄን ሳይሆን በዋናነት ሰብዓዊ መብትን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጠይቅ መሰረታዊ ነጥብ አንስቶ ነው ህብረተሰቡን በፅናት ለ 4….አመታት ሰላማዊ ትግልን ሲያካሂድ የቆየው አሁንም እያካሄድ ያለው….. ይህን ውለታ ማንኛችንም ቢሆን መርሳት የለብንም እውነት አገር ወዳድ ማንነት ካልለን! በክርስቲያኖች ስቃይ የሚደሰት ሙስሊም እንዲሁም በሙስሊሞች ስቃይ የሚደሰት ክርስቲያን በተለይ አሁን ዘመን ላይ ይኖራል ብዬ ተስፋ አላደርግም ምክንያቱም መንግስት ተብየው መጅሊስ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሲኖዶሱንም ገብቶ እየዋኘበት ነው በደላችን አንድ አድርጎናልና ከዚህ ቡሃላ እንኳን ተውን በቃ እንዋደድበት ከ ሺህ አመት በፊት በሰላም ኖረናል አሁን መጥታችሁ ፍቅርን እናስተምራችሁ አትበሉን (ፀሃፊው!)
  በነገራችን ላይ አንድ ማሳያ የሚሆነን ለምሳሌ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የሆነው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ይሄው ከእስር ከመፈታቱ ከተወሰነ ቀናት ቡሃላ ወንድም ሃብታሙ አያሌውን ሂዶ በመጠየቅና በመዘየር አንድነቱን አሳይቷል ይሄ ቦታ ቢበቃኝና ብዙ ብዙ ማንሳት በቻልኩ ጥሩ ነበር ብስል ግን አስግትቱኝ እንጂ አጥግቡኝ ስለማይል ፍርዱንና ትዝብቱን ለአንባቢ ትቼ እኔ እዚሁ ላይ አስተያየቴን ልቋጭ
  አላህ ኢትዮፕያችንን የሰላም የፍቅር የመተሳሰብና የመፈቃቀር የእኩልነት ሃገር ያድርግልን ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለይም በየ እስር ቤቱ የሚማቅቁ ኢትዮጵያኖችን ሁሉ በእዝነትህ በራህመትህ ከእስር ነፃ አድርግልን አዋደን አፋቅረን ምቀኛችንንም ሁሉ ከመሃከላችን አርቅልን አሚን! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ወሰላሙ አለይኩም