ሳይገንዙት (ሰይፉ ኣዳነች ብሻው – አትላንታ)

(ግጥም)

ውሸት ያልታከተው

ውሸት አስተምሯቸው

በውሸት ክኗቸው

በክብር ያልሞተው

ዛሬ ዋሽተው፣ ዋሽተው

ቋንጣውን ሊያቀርቡ ነው

ወይ ያኔ! ይኹን ዛሬ!

ውሸት ሞተ አሉኝ ውሸትን ማን ያምናል

ውሸት ከሞተማ እውነት ይታወቃል

በርግጥ… ውሸት ከሞተማ ቀባሪው እውነት ነው

እውነት ስለሆነ ለዘላለም ቀሪው

እንግዲህ እውነት ተነሺ ለቀብር

የእውነት ቀኑ ደርሶ ውሸት ሲቀበር!!!

ሳይገንዙት

ሳይፈቱት

ሄዱ ጥለውት

አይ ሞት!

ሞት አይዋሹበት

ሞትም እንደ እውነት!

ውሸት አያውቅበት ሞት!

ቢቀብሩት ቢቀብሩት

የማይደብቁት

ይወጣል እንጂ እንደ እውነት!!!

በረሃ ይሁን ጫካ፣ሜዳ ወይ ከአለት

አፅሙ እስካለ ድረስ ባይኖረውም ሃውልት

መቃብር ነው የሞት እውነት

ያሳያልና ከወደቀበት ማን እንዳለበት

መቃብር አይደብቀው

ክፋት መልካም አይሆን

ተንኮል መልካም አይሆን

መጥላት መልካም አይሆን

መቃብር አይሸፍነው ተግባርን፣ እውነትን

ስም ከመቃብር በላይ ኗሪውን

እልል የሚያሰኝ ጊዜ መጣ

ሰው አስከሬኑ ሲወጣ

በወያኔ ጣጣ

አይ የኢትዮጵያ ዕጣ!!!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 1, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.