ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ (+DW audio)

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እርማጃና ተቃዉሞዉ

አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።

መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ፤ አስፋዉ ሚካኤል መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
Thema: Äthiopien - Protest gegen Saudi Arabiens Aktion gegen Äthiopier Einwanderer
Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher (Addis Korri.) 15.11.2013

ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ።ትናንት እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።

Thema: Äthiopien - Protest gegen Saudi Arabiens Aktion gegen Äthiopier Einwanderer
Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher (Addis Korri.) 15.11.2013

ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ።ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር —የሚል ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር/ አበበ ፈለቀ

ነብዩ ሲራክ/ ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

AUDIOS

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.