“ሲዋን” የተሰኘ አዲስ መጽሃፍ ለንባብ በቃ

በጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኽኝ የተጻፈው “ሲዋን” የተሰኘው አዲስ መጽሃፍ በዩናይትድ ስቴትስ ጆርጂያ አትላንታ ታትሞ ለንባብ በቃ። መጽሃፉ ዋና የታሪኩ ሂደት የሚያጠነጥንበት መስመር ከኢትዮጲያ ሶማሊያ ከዚያም ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገውን አስቸጋሪ የስደት ጉዞ ታሪክ የሚዳሥ ሲሆን ሙሉ የመጽሃፉ ታሪክ በ እውነተኛ ሂደት ላይ የሚያተኩር መሆኑም ታውቆዋል።

መጽሃፉ 297 ገጾች ያሉት ሲሆን አስከፊውን የአረቢያን ባህር የጀልባ ጉዞ አሰቃቂነት ይተርካል። በሌላ በኩልም ደራሲው ከሃገር በወጣበት የምርጫ 97 ማግስት እና የምርጫ 97 ዋዜማ እውነተኛ ሂደት እና እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ በመረጃ አስደግፎ ትውስታውን የገለጸበት የመጽሃፉም ክፍል የሚዳሰሰው ሌላው የታሪክ ሂደት እንደሆነ ለማወቅ ተችሎዋል።

በሌላ በኩል ምንም እንኩዋን የመጽሃፉ ደራሲ ከመንግስት በተቃጣበት አደጋ ሳቢያ ሃገር ጥሎ ለመሰደድ የበቃበትን ሂደት በታሪኩ ውስጥ ለአንባቢያን ያቅርብ እንጂ ፡ በስደቱ ጎርፍ ውስጥ የሚያልፉ በርካታ ኢትዮጲያውያንን ታሪክ የዳሰሰ እና ለማመን የሚያዳግቱ ግን የመጽሃፉ ደራሲ በአይኑ የተመለከታቸውን የሰባ አንድ ሰአታት የየብስ ላይ ጉዞ እንደዚሁም ዘግናኙን የአርባ አንድ ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ ከባለታሪኮቹ አጋጣሚዎች ጋር ለንባብ አብቅቶዋል። በመጽሃፉ ውስጥ ከቀረቡት ታሪኮች ውስጥ በባህር ጉዞ ላይ እያሉ ስለሚሞቱት ስደተኛዎች ፤ እንዲሁም ከኢትዮጲያ የጠረፍ ከተማዎች አንስቶ እስከ ሶማሊያ ድረስ በሰው አዘዋዋሪዎች ዜጎች ላይ የሚደርሰው በተደጋጋሚ በውጪ ሚዲያዎች በግርድፉ የሚቀርቡ ወሬዎች ተተንትነው የቀረቡበትም ሂደት እንዳለ ከመጽሃፉ ለመረዳት ተችሎዋል።

ደራሲው ይህንን መጽሃፍ የጻፈበትን ሂደት እና እውነታ አስመልክቶ መጽሃፉ ለህትመት ከመብቃቱ በፊት  መጽሃፉን ለማንበብ የታደሉት ሁለቱ እውቅ ጋዜጠኛዎች እና ጸሃፍት ተስፋዬ ገብረ አብ እና ክንፉ አሰፋ በመጻሃፉ ጀርባ ላይ በሰጡት አስተያየት በታሪኩ መገረማቸውን ጠቅሰው አስተያየታቸውን አቅርበዋል። “ሲዋን” የተሰኘው መጽሃፍ በአሁኑ ወቅት በአትላንታ ታዋቂ ሃበሻ ማርቶች በመሸጥ ላይ ሲሆን እንደዚሁም በላስቬጋስ ፤ በዳላስ ፤ በካሊፎርኒያ ፤ በቺካጎ አውሮፓ ጣሊያን ሮም፤ በፈረንሳይ ፓሪስ በመከፋፈል ላይ ሲሆን በቀጣይም ወደሌሎች የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተማዎች እንደሚሰራጭ ለማወቅ ተችሎዋል። መጽሃፉን ለማግኘት እንዲሁም ለማከፋፈል የሚፈልጉ ክፍሎች በዚህ ስልክ ቁጥር መጠየቅ ይችላሉ።

የስልክ ቁጥር 404 610 6954
Email: daniel_mb1232000@yahoo.com

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 16, 2012. Filed under VIDEO. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.