ሰብአዊ መብት ለሰብአዊያን – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በዓለም ዙርያ ያሉትን አንባቢዎቼን 2013 የደስታና የብልጽጋና ዓመት ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ላለፉት ያልተቋረጡ 300 ሳምንታት ያህል ጦማሮቼን ለተከታተሉ ሁሉ፤ከልብ የመነጨ አክብሮቴንና ምስጋናዬን እገልጻለሁ፡፡ ከኢትዮጵያና ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ለተቸረኝ ማበረታታት ምስጋናዬ ይድረስልኝ፡፡

አንባቢዎቼን፤ በኢትዮጵያና በዓለም ላይ ሁሉ የተደፈሩ ሰብአዊ መብቶችን ለሁሉም ሰብአዊ ፍጡራን እንዲዳረሱና እንዲከበሩ የመጠራሪያና የማንቂያ ደወል በአፍሪካና በዓለማቱ ሁሉ እንደውል እላለሁ፡፡ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ አንዳሉት “በማይበጠስ የአንድነት ሰባዊ ሰንሰለት ተሳስረናል፡፡ በአንድ አይነት እጣ ፈንታ ተያይዘናል:: አንዱን በቀጥታ የሚያጠቃው ሌላውንም በተዘዋዋሪ ደግሞ አይተወውም፡፡

አንባቢዎቼን፤ በሎርድ አልፍሬድ ቴኒሰን የረቀቀ ለዛ ባለው ግጥም (“እንጠራራ፤ ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ”) አሮጌውን ዓመት በመሰናበት አዲሱን እንቀበል በማለት አጠይቃለሁ::

Read full story in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 1, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.