ሰበር ዜና: በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሄደ

ኢ.ኤም.ኤፍ. – የኤርትራ መከላከያ ሰራዊተ በዛሬው እለት (ሰኞ 21 ጃንዋሪ) በፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ መፈንቅለ-መንግስት ሙከራ ማድረጉን ኢ.ኤም. ኤፍ. ከአስመራ በስልክ አረጋግጧል:: ሰራዊቱ በአሁን ሰዓት ማስታወቂያ ሚኒስትሩን የተቆጣጠረ ሲሆን እስካሁን ምንም አይነት ደም መፋሰስ እንደሌለ ዘጋቢያችን ገልጿል::

ኢሳያስ አፈወርቂ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም::

ምንጮች እንደሚሉት ኢሳያስ አፈወርቂ ለስራ ጉብኝት ምጽዋ ሲሆኑ ከአስመራ-ምጽዋ የሚወስደው መንገድም በወታደሮች ዝግ ሆኗል::

ወታደሮቹ በተለይ የኤርትራ ጋዜጠኞች ምንም እንቅስቃሴ እንዳያድርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ጋዜጠኛዋ የኢሳያስ አፈወርቂ ልጅም እንደታገተች ተገልጿል::

እንደ ሪፖርተራችን ዘገባ ህዝቡ እንዲረጋጋነ እቤቱ እንዲቀመጥ ሰራዊቱ እየተናገረ ሲሆን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሙሉ ተቋርጠዋል::

ምንም ደም መፋሰስ ሳይኖር ማስታወቂያ ሚ/ርን እስከመቆጣጠር መድረስ ያልተለመደ መፈንቅለ-መንግስት ነው::

የአፍሪካ ጥናት አኤክስፐርት የሆነው ማርቲን ፕላውት ዲፕሎማቲክ ምንጮችን በመጥቀስ መፈንቅለ መንግስት እየተካሄደ መሆኑን በድረ-ገጹ ጽፏል:: ከፈረንሳዩ ኤ.ኤፍ.ፒ. በስተቀር አለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዜናውን አልዘገቡትም::

ዝርዝር ዘገባውን እየተከታተልን እናቀርባለን::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 21, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.