ግብጽ ነጻ ወጣች: ሆስኒ ሙባረክ 40-70 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈው ጠፉ

የ82 አመቱ የግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባረክ ከ32 አመት የስልጣን ዘመን በኋላ በዛሬው እለት ስልጣን የለቀቁ ሲሆን ከነቤተሰቦቻቸው እንደጠፉ ማምሻውን ይፋ ሆኗል:: ሞባረክ ስልጣን እንዲለቁ የግብጽ ህዝብ ላለፉት 17 ቀናት የተደራጀና ያልጠቋረጠ ተቃውሞ ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል::

በሚሊዮን የሚቆጠር የግብጽ ህዝብ በደስታ የካይሮን ከተማ አጨናንቋታል::

የ82 አመቱ አንባገነን መሪ ስልጣን መልቀቃቸውን እና ስልጣኑን ለወታደሩ ከፍተኛ ምክር ቤት መሰጠታቸውን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ኦማር ሱለይማን በሃገሪቱ ቴሌቭዥን አስታውቀዋል::

ሙባረክ ከመኖርያ ቤተመንግስታቸው በሁለት ሄሊኮፕተሮች የተወሰዱ ሲሆን አሁን የት እንዳሉ አይታወቅም:: በርካታ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት ሙባረክ ወደ አረብ ኤሚሬት ተጉዘዋል::

የእንግሊዙ ጋርዲያን ጋዜጣ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገሮች ምንጮችን በመጥቀስ እንደዘገበው ሙባረክ እና በተሰቡ ከ $ 40 እስከ $ 70 ቢሊዮን ዶላር እንዳካበቱ ገልጿል:: ይህ መጠን ፎርቱን መጽሄት ካወጣቸው የአለም ቁንጮ ሃብታሞች: ከሜክሲኮው ካርሎስ ስሊም ($54 ቢሊዮን) እና ከአሜሪካዊው ቢል ገትስ ($53 ቢሊዮን) ይበልጣል::

ተያይዞ በደረሰን ዜና ሙባረክ ከግብጽ ዘርፎ በስዊዝ ባንክ ያስቀመጠውን 70 ቢሊዮን ዶላር የስዊዝ መንግስት ያገደበት መሆኑን ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል:: ዜናው ሙባራክ በስልጣን ረጅም- እድሜ ብቻ ሳይሆን: ከአለም ሃብታሞችም በአንደኝነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ይጠቁማል::

…ይህ አይነቱ ህዝባዊ ትግል እና ድል በአንባገነን ገዢዎች ስር ላሉ ህዝቦች የነጻነት ተስፋ የፈነጠቅ ሲሆን በኢትዮጵያም እንደሚቀጣጠል በስፋት እየተወራ ነው::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 11, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.