ሰበር ዜና፣ የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎች ላይ አደጋ ተጣለ

Breaking News (16 July 2009) – Unidentified agents are attacking members of Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Church who have expressed disagreements with Patriarch Paulos by his despotic decisions, an online source close to the church revealed today. According to the source, Abune Rufael and Abune Ephifamios are among the bishops who are physically attacked and taken to unknown locations. Read full in Amharic…
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009) – ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ መጣላቸው ተሰማ። 

የደጀ ሰላም ምንጮች እንደተናገሩት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለፈው ጊዜ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የብፁዓን አባቶችን መኖሪያ በመደብደብ፣ በር ገንጥሎ በመግባት አደጋ ማድረሳቸው ሲታወቅ ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት አባቶች ላይ የደረሰው አደጋ ምን እንደሆነ፣ የተጎዱትስ አባቶች ምን እንደገጠማቸው አልታወቀም። ምንጮቻችን እንደተናገሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሲጮሁና “አድኑኝ” ሲሉ ተሰምተዋል ተብሏል።

ፓትርያርኩን በመቃወሙ ዘርፍ ስብሰባዎችን ሲመሩ የሰነበቱት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖሪያ በር ከተሰበረ በሁዋላ ብፁዕነታቸው የመኝታ ቤታቸውን በር ቆልፈው ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ማንነታቸውን ለጊዜው ያላወቅነው አንድ አባት ግን ችግር ሳይደርስባቸው አልቀረም። እኚሁ አባት “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው፤ ታፍነው ሳይወሰዱ አልቀሩም” ሲሉ ምንጮቻችን ጥቆማ ሰጥተዋል። ይህንኑ ያወቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መግባታቸውም ታውቋል።

በሌላም በኩል ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውጪ ቃሊቲ አካባቢ ባለው መኖሪያቸው የሚኖሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጥቃቱ ኢላማ የነበሩ ሲሆን አደጋ ጣዮቹ በራቸውን በተደጋጋሚ ከደበደቡ በሁዋላ፣ በጥበቃ ሠራተኞቻቸው መኖር ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ብፁዕነታቸውም ወደ ፖሊስ ዘንድ በመሄድ ቃላቸውን ሰጥተው ተመልሰዋል።

የዛሬው አደጋ ኢላማ የሆኑት አባቶች የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎችና በዛሬው ስብሰባ ላይ ጠንካራ ሐሳብ የሰነዘሩት ናቸው ተብሏል። ነገሩ በርግጥም በተባለው መልኩ ተፈጽሞ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ አደጋ ላይ የመሆኗ የመጨረሻ ምልክት ይሆናል ማለት ነው።

ቀሪውን እንደደረሰን እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 16, 2009. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.