ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በድምቀት ተከናወነ (የሰልፉን ፎቶዎች ይዘናል)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልሳለን›› በሚል ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ይኸው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት የተከናወነ መሆኑን አሁን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል። እንደዘገባው ከሆነ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ፤ በተለይ በመብራት መጥፋት፣ በውሃ እጦት እና በኔትዎርክ መቆራረጥ ምክንያት የደረሰበትን ብሶት አሰምቷል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ህዝቡ ውሃ እና መብራት በፈረቃ የሚያገኝ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ከ15 ቀናት በላይ ምንም አይነት ውሃና መብራት ሳያገኙ የሚቆዩ አሉ። ዛሬ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍም ይኸው ብሶት በህዝቡ ሲስተጋባ ነበር። ህዝቡ በህብረት ሲያስተጋባ ከነበረው መፈክር መሃልም…
“ውሃ ጠማን!”
“ጨለማ ዋጠን!”
“ትራንስፖረት ቸገረን!”
“ዘመድ ናፈቀን!”
“መንግሥት የለም ወይ?” የሚሉት ይገኙበታል።

ይህንን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማርገብ ሲባል፤ ኢህአዴግ መራሺ ኢቲቪ በተከታታይ እና በተደጋጋሚ፤ “የውሃ እና የመብራት መቆራረጡ ጊዜያዊ መሆኑን እና ኔትዎርኩም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተሻሻለ ነው” በማለት ልዩ ዝግጅት ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን፤ እንዲህ ያለው የኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ያላሸነፈው የአዲስ አበባ ህዝብ ግን በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሏል።
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት አንዱና ዋነኛው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እየተጻረረ ያለውን የኢህአዴግ ስርአት ህዝቡ ተቃውሞታል። ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ የሚታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በዚህ ሰልፍ ላይ ጥያቄ ቀርቧል። ገዥውን ፓርቲ ስለተቹና ለህዝባቸው መረጃ ስለሰጡ ብቻ የሚታሰሩትን አስመልክቶ፤ ድርጊቱ “ህገ ወጥ እርምጃ ነው” በማለት አውግዟል። የእስክንድር ነጋ እና የርእዮት አለሙን ፎቶ ይዘው በመውጣት ጭምር ነው ተቃውሟቸውን ያሰሙት። “ነጻነት እንፈልጋለን” የሚሉትና “ፍርሃትን ያላሸነፈ፤ ባርነት ልብሱ ነው! ፍትህ ናፈቀን፣ ውሸት ሰለቸን፣ ገዥው ፓርቲ ስልጣኑን ያስረክብ፣ የኑሮ ውድነት መፍትሄ ይሸል፣ ሙስና ይቁም፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች፣ ፖለቲከኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!! …የሚሉት መፈክሮች በተቃዋሚው ህዝብ በኩል ተስተጋብቷል።

በሳምንቱ ውስጥ የህዝብን መብት ለማስመለስ ለተጠራው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 50 ያህል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በህገ ወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ አርብ እለት የፓርቲው ሊቀመንበር (ምሽቱን ተፈትተዋል)፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ አክቲቪስቶችና ሌሎች ጋዜጠኞችም መታሰራቸው ይታወሳል። ይህም ሁሉ ሆኖ ፓርቲው እና ደጋፊዎቹ ዛሬ እሁድ ጠዋት ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው፤ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ለ-ኢ.ኤም.ኤፍ የደረሱት ዘገባዎች ያስረዳሉ።

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ያሉትን ፎቶዎች ይመልከቱ። ወደመጨረሻዎቹ ፎቶዎች ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ከፖሊሶች ጋር ሲጨቃጨቁ ይታያል። የጭቅጭቁ መንስኤ… ፖሊስ ሰልፉን አድዋ ድልድይ ላይ ለማስቆም በመሞከሩ ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 27, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በድምቀት ተከናወነ (የሰልፉን ፎቶዎች ይዘናል)

 1. ትዝብት

  April 27, 2014 at 11:12 AM

  ከታላቅ ይቅርታ ጋር!! ከዚህ በታች ለምሰጠው የግል አስተያየቴ!!
  በቅድሚያ የማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አይደለሁም: አስፈላጊና አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ ግን የተወሰን ጉዋደኛሞች ተወያይተን የገንዘብ ድጋፍ እንደአስፈላጊነቱ በማሰባሰብ እንለግሳለን(ለሁሉም ፓርቲ);;
  ወደዋናው ሃሳቤ ሳመራ እንዴት ከሃምሳ በላይ አባላቶቹን አስሮ ሊቀመንበሩን ብቻ ወያኔ ሊፈታ ቻለ? ታስሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ወደ እሥር ቤት እየተወሰደ ፖሊስ ለእሱ ብቻ ስልክ ፈቅዶ ለኢሳት ሪፖርት ሲያደርግ ዝም አለው?(ፍጹም ወያኔ አድርጎት የማያውቀውን ነገር?) ጠርጥር!! አንድ የሚሸት ነገር ይሰማኛል!!
  ደግሞስ አላማውና ትግሉ ወያኔ በኢትዮጵያና በህዝብዋ የሚፈጽመው ግፍ በቃ ከሆነ! ሰላማዊ ሰልፍ እንኩዋን ከሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር ተባብሮ መውጣት የማይችልበት ምክንያት ምንድን ነው?? ከሃገር ጥቅም ይልቅ የራስ ክብርና ዝናን ለማትረፍ?? ወይስ ለጠላት የከፋፍለህ ግዛው መርሆውን ማስፈጸም??
  ወይስ አጉል ባህል ሆኖ ጀብደኝነትና ያለ እኔ አዋቂ ለዓሳር ነው??
  አባቶቻችን ግን በአንድ ጥላ ሥር ሆነው በሃገርና በሚስት አቀልድ የለም ብለው ጠላትን በአንድ ላይ ሆነው ድል አድርገውኣል!!!!!
  እሥራኤልን ብትመለከቱ; በሃገር ጉዳይ ላይ ከመጡባቸው ከመሪው እስከ ህዝቡ ግራ ክንፍ ቀኝ ክንፍ የሚባል ነገር የለም ሁሉም የመጣብባቸውን የሀገር ጠላት አንድ አካልና አምሳል በመሆን ያለምንም ልዩነት የምጣውን ጠላት ይመክታሊ:: በሃገራቸው ቀልድ የለም::
  ለወያኔ እድሜ መራዘም ዋናዎቹ የተቃዋሚ ፖርቲዎች መሆናችሁን ተገንዝባችሁ! ቀን ቀንን እየወለደ ሲሄድ የወያኔ እድሜም በዛው ልክ በሚራዘሙ የታሪክ ተወቃሽ መሆናችሁን እንዳትዘነጉት!!!

  ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ያስባት!!!! አሜን!!!!!

 2. ትዝብት

  April 27, 2014 at 11:20 AM

  ከታላቅ ይቅርታ ጋር!! ከዚህ በታች ለምሰጠው የግል አስተያየቴ!!
  በቅድሚያ የማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አይደለሁም: አስፈላጊና አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ ግን የተወሰን ጉዋደኛሞች ተወያይተን የገንዘብ ድጋፍ እንደአስፈላጊነቱ በማሰባሰብ እንለግሳለን(ለሁሉም ፓርቲ);;
  ወደዋናው ሃሳቤ ሳመራ እንዴት ከሃምሳ በላይ አባላቶቹን አስሮ ሊቀመንበሩን ብቻ ወያኔ ሊፈታ ቻለ? ታስሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ወደ እሥር ቤት እየተወሰደ ፖሊስ ለእሱ ብቻ ስልክ ፈቅዶ ለኢሳት ሪፖርት ሲያደርግ ዝም አለው?(ፍጹም ወያኔ አድርጎት የማያውቀውን ነገር?) ጠርጥር!! አንድ የሚሸት ነገር ይሰማኛል!!
  ደግሞስ አላማውና ትግሉ ወያኔ በኢትዮጵያና በህዝብዋ የሚፈጽመው ግፍ በቃ ከሆነ! ሰላማዊ ሰልፍ እንኩዋን ከሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር ተባብሮ መውጣት የማይችልበት ምክንያት ምንድን ነው?? ከሃገር ጥቅም ይልቅ የራስ ክብርና ዝናን ለማትረፍ?? ወይስ ለጠላት የከፋፍለህ ግዛው መርሆውን ማስፈጸም??
  ወይስ አጉል ባህል ሆኖ ጀብደኝነትና ያለ እኔ አዋቂ ለዓሳር ነው??
  አባቶቻችን ግን በአንድ ጥላ ሥር ሆነው በሃገርና በሚስት አቀልድ የለም ብለው ጠላትን በአንድ ላይ ሆነው ድል አድርገውኣል!!!!!ት
  እሥራኤልን ብትመለከቱ; በሃገር ጉዳይ ላይ ከመጡባቸው ከመሪው እስከ ህዝቡ ግራ ክንፍ ቀኝ ክንፍ የሚባል ነገር የለም ሁሉም የመጣብባቸውን የሀገር ጠላት አንድ አካልና አምሳል በመሆን ያለምንም ልዩነት የምጣውን ጠላት ይመክታሊ:: በሃገራቸው ቀልድ የለም::
  ለወያኔ እድሜ መራዘም ዋናዎቹ የተቃዋሚ ፖርቲዎች መሆናችሁን ተገንዝባችሁ! ቀን ቀንን እየወለደ ሲሄድ የወያኔ እድሜም በዛው ልክ በሚራዘሙ የታሪክ ተወቃሽ መሆናችሁን እንዳ”ትዘነጉት!!!

  ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ያስባት!!!! አሜን!!!!!