ሰላማዊ ሰልፉ በመጨረሻ ተፈቀደ (ቦታ እና ቀኑ ተቀይሯል)

Demo_addisdemo_addis_2ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ማወቅ ለሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ አሳውቆ ነበር። ሆኖም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ደብዳቤውን ቢያቀርብም፤ “ደብዳቤ እንዳንቀበል ከበላይ ታዘናል” በማለት በቃል ተመሳሳይ የአንቀበልም መልስ ሰጥተዋል፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ከፓርቲው በኩል ሦስት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤቱ ደግሞ ሦስት ሰዎች የአይን ምስክርነት ባሉበት በሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ ኃላፊ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ ደብዳቤው በፖስታ ቤት በኩል በሪኮመንዴ እንዲደርስ ተልኳል፡፡

በዚህም መሰረት፤ ሰልፉን ለማድረግ በህግ በኩል የጎደለ ምንም ነገር ባለመኖሩ ሰልፉ በታቀደው ቦታና ስዓት የሚካሔድ መሆኑን ግንቦት 15 ቀን፣ 2005 አሳውቆ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ከንቲባ በዛሬው እለት በተሰጠ ገለጻ መንግስት 50ኛውን የአፍሪካ ህብረት በአል ለማክበር በአሁኑ ግዜ ከፍተኛ የጸጥታ ሰራተኞች መድቦ በመስራት ላይ በመሆኑ ከፓርቲው የቀረበልንን ጥያቄ ለማስተናገድ የጸጥታ ሰራተኞች እጥረት አለብን ብለዋል ፡፡ይህም በመሆኑ የተቃውሞ ሰልፉ ቀንና ቦታ እንዲለወጥ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም የዚህን ጥያቄ ተገቢነት ከሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ስነስርአት አዋጅ ቁጥር 3/1983 አንጻር በመመርመር ተገቢ ሆኖ ስላገኘው የተቃውሞ ሰልፉ ግንቦት 25/ 2005 አ.ም. በኢትዮ-ኩባ አደባባይ ከጠዋቱ 4 ሰአት- 8 ሰአት እንዲሆን በመወሰን ከመንግስት የእውቅና ማሳወቂያ ደብዳቤውን ተቀብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት በኩል ፈቃድ የተሰጠ መሆኑ በቴሌቪዥን ጭምር ተገልጿል። የፈቃዱም ደብዳቤ እንዲህ የሚል ነው።
ቁጥር አአ\ከጽ\10\30.4\166
ቀን 15\9\05
ለሰማያዊ ፓርቲ
(ሰማያዊ)
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የተጠየቀውን ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና መስጠቱን ስለማሳወቅ
ፓርቲያችሁ በቁጥር ሰማ/03/2005 ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓም. በፃፈው ደብዳቤ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፋችሁን ግንቦት 24 ቀን 2005 ዓም. ህጉ በሚፈቅደው ቦታ ማካሄድ እንድትችሉ እውቅና የተሰጣችሁ መሆኑን እንድታወቁት እየገለጽን በግልባጭ የተገለጸላችሁ አካላትም ሰላማዊ ሰልፉን እውቅና የተሰጣቸው መሆኑን አውቃችሁ ተገቢው ትብብር ታደርጉላቸው ዘንድ እናሳስባለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
ማርቆስ አንተነህ ማንደፍሮ
የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ
ማሳወቂያ ኦፊሰር
የማይነበብ ፊርማና ምህተም
ግልባጭ ፡-
. ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት
. ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
. ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
በመሆኑም በሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 24 ቀን፤ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ሳይሆን፤ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ፓርቲ በድምቀት ይከበራል ተብሎ ይጠበቃል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ሰላማዊ ሰልፉ በመጨረሻ ተፈቀደ (ቦታ እና ቀኑ ተቀይሯል)

  1. ኡስህዪ ቭጅይ ግንብት 20 ክን 2005! ምንግስት ግልንት ትውድድ

    May 25, 2013 at 11:11 PM

    ጥህ ብህርፍት ይሁን ምንግስት ትውድሁ 2005!;