ሪፖርተር ሶማሊያ ስለተከሰከሱት አውሮፕላኖች ሲዘግብ ስለመንሰኤው አለመጠየቁ – በክፍሉ ሁሴን

የአቶ አማረ አረጋዊ ጋዜጣ ብቻ እንዲዘግበው በተፈቀደው መሰረት በቀደም ሶማሊያ ላይ ተከስክሶ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አንቶኖቭ 12 የተባለው ሩሲያ ሰራሽ አውሮፕላን አደጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው አደጋ መሆኑን እ.ኤ አ በኦገስት 11,2013 ባሰፈረው ዘገባው ይነግረናል።ሌሎች ይህን ቢዘግቡት ምስጢር በማባከን የ”ብሔራዊ ደህንነትን”ሆነ ብሎ አደጋ ላይ በመጣል ወይም በዚያ በፈረደበት የሽብርተኛ ፍርደ ገምድል ሕግ ዘብጢያ ይወርዱ ነበር።ያም ሆነ ይህ ሪፖርተር በአንቶኖቩ ላይ ይህ አደጋ ከመከሰቱ ጥቂት ቀናት በፊት ሌላ ኤል 100 የተባለ የ”አየር ሃይሉ”አውሮፕላን እዚያው ሶማሊያ ተከስክሶ መሰባበሩንና አብራሪዎቹም የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሆኑ፤የዚያ አውሮፕላን ዳፋም ስብርባሪውን ሊያመጣ ለሄደው ለዚህኛው አንቶኖቭ እንደተረፈው ዘግቧል።በነፃ ጋዜጣ ስም የቁርጥ ቀን የወያኔ አፈ ቀላጤነቱን የማይዘነጋው ሪፖርተር የ”አየር ሃይሉ”አውሮፕላኖች እንደደርግ ጊዜ ሳይተኮስባቸውና ቦምብ ሳይቀበርባቸው ባገር ጤና በየሳምንቱ በየሄዱበት ባፍጢማቸው ለምን እንደሚደፉ አጠያይቆ ሊዘግብ አልሞከረም።እሱ ባይዘግብ እኛ እንጠያይቅና የመጠይቃችንን ውጤት እንመልከተዋ! Read story in PDF…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 19, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ሪፖርተር ሶማሊያ ስለተከሰከሱት አውሮፕላኖች ሲዘግብ ስለመንሰኤው አለመጠየቁ – በክፍሉ ሁሴን

  1. Pingback: ሪፖርተር ሶማሊያ ስለተከሰከሱት አውሮፕላኖች ሲዘግብ ስለመንሰኤው አለመጠየቁ – በክፍሉ ሁሴን | Ethio News Explorer