ሦስተኛው የአስገደ ልጅ ታሰረ! (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

ክብሮም የተባለ የአስገደ ገብረስላሴ ልጅ ጥቅምት 6, 2006 ዓም ጠዋት በፖሊስ መታሰሩ ታወቀ። ልጁ የታሰረው ከጓደኞቹ ጋር ኳስ ሲጫወት እንደሆነና ከሱ ጋር ሲጫወቱ ከነበሩ አምስቱም ታስረዋል። ክብሮም ከአስገደ ልጆች ሦስተኛ ተበዳይ (ታሳሪ) መሆኑ ነው። ልጁ ከታሰረ እስካሁን ድረስ ሦስት ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን ወላጅ አባቱ እንዳያገኘው ተከልክሏል። የታሰረበት ምክንያትም ለወላጅ አባቱ እስካሁን አልተነገረውም። እኔ ከወደ እስርቤቱ አከባቢ ያገኘሁት መረጃ እንደሚያመለክተው ግን ልጁ የታሰረው የተለያየ ዓይነት ቁልፍ በኪሱ በመገኘቱ… ተጠርጥሮ ነው
እስካሁን የታሰሩት የአስገደ ልጆች:
(1) አሕፈሮም አስገደ (እስካሁን ያለ ፍርድቤት ዉሳኔ እንደታሰረ ነው)
(2) የማነ አስገደ (ቆሻሻ ክፍል ዉስጥ ታስሮ ከታመመ በኋላ ተፈቷል)
(3) ክብሮም አስገደ (ትንሹና አዲሱ እስረኛ)አቶ አስገደ ገብረስላሴ ዛሬ አነጋግሬው ነበር። ተናዷል። በሱ የፖለቲካ አቋም ምክንያት ልጆቹ ሲሰቃዩ ማየቱ አሳዝኖታል።

አስገደ “እዞም ሰባትባ ክሽፍት ድዮም ደልዮምኒ? (እነዚህ ሰዎች እንዲሸፍት ነው የሚፈልጉኝ?)” አለ። “የምትሸፍትበት ግዜማ አልፏል፤ አሁን በቆም መስዋእት መሆን ነው” አልኩኝ በልቤ።

አቶ አስገደ እና የታሰሩት ልጆቹ

አቶ አስገደ እና የታሰሩት ልጆቹ


“እነ አስገደ ገብረስላሴ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ የታገሉ፣ መስዋእት የከፈሉ አባቶች በሰላም መኖር ያልቻሉ እኔ (በዕድሜ ምክንያት) በትጥቅ ትግሉ ምንም አስተዋፆ ያላደረግኩ ህወሓት ጥሩ ይሆንልኛል ብዬ ማሰብ እንዴት ይቻለኛል” ብዬ አሰብኩ። አዎ! ‘ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ነፃነት ታግያለሁ’ ይለናል። ግን እንኳን ለትግራይ ህዝብ ነፃነት ይቅርና ለራሳቸው ለህወሓት ታጋዮች ነፃነትም አልቆመም። ታጋዮቹ እንኳን በነፃነት ሊኖሩ ሳይታሰሩ መኖርም አልቻሉም።

ህወሓቶች የራሳቸው ታጋዮች እንዲህ እያሰቃዩ የዋሁ የትግራይ ህዝብ ህወሓቶች ትግርኛ ተናጋሪ በመሆናቸው ብቻ ከጠላት ይጠብቁናል ብሎ ያስባል። እነሱ ግን ለስልጣናቸው የሚረዳ ብቻ ነው የሚተባበሩ። ማንኛው አምባገነን ስርዓት ባርያ ሁነው ካገለገልከውማ ምንም ኮ አያደርግህም። ለደርግ ስርዓት ባርያ ሁነን ለማገልገል ብንነሳ ኑሮ አይገድለንም ነበር። ግን ባርያ ከመሆን የባሰ ግድያ የለም። ስለዚህ ባርያ ሁኖ የሚያገለግል ሁሉ ህይወት እንደሌለው ይቆጠራል።

ለገዢዎች ባርያ ሁኖ ያለ ነፃነት ከማገልገል ለነፃነት እየታገሉ መሰዋት መሆን ይሻላል።

አቶ አስገደ ገብረስላሴ

አቶ አስገደ ገብረስላሴ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 20, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.