ምንሊክን በጎሪጥ (ከባዩ በየነ ኪዳኔ- ቶሮንቶ ካናዳ)

መኮንን ረጋሳ star bucks የሚሉት ቡና መጠጫ ፀጥ ባለ ክፍል reserve ባስደረገው ጠረጴዛ ላይ ትንሿን ኮምፒዩተር አስቀምጦ ከወንበሩ ላይ አረፍ አለ። ኢትዮጵያን እንደቡና ሊያሸታት ሲፈልግ ካበሻ ሬስቶራንት ቀጥሎ የሚያዘወትረው star bucksን ሰለሆነ አስተናጋጆቹ ያውቁታል።

መኮንን ረጋሳ በናቱ ትግሬ ነው። እናቱ ግን የሃማሴንም የጎንደሬም ደም እንዳላቸው ያወሩ ነበር። አባቱ ረጋሳ ደሞ ያው ረጋሳ ናቸው፤ የለም የለም እሳቸውም ቢሆኑ ‘የሶዶ ጉራጌነቴ ያመዝናል’ እያሉ ዘራቸውን ሲያስቆጥሩት ነበር። እንግዲህ ይህን ሁሉ የተደበላለቀ እሱነቱን ይዞ ነው ስለ አድዋ በዓል ትንሽ ነገር ሊከትብ አስቦ የተቀመጠው። የአድዋን ውሎ በዓይነ-ህሊናው እየቃኘ ሳለ የሃሳብ ጎርፍ ጠለፈው። በሃሳብ መጠለፍ – የሥደተኛ አበሻ ግብር፣ ዕዳ፡ ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ‘ተማር’ ብለው ፈረንጅ አገር ሲልኩት ምኞቱ አገሩን የሚያስነክሳትን የደህነት እሾህ መንግሎ መጣል ነበር።፡ተዛ ወዲህ አገሩን ያየው አንዴ ብቻ ነው – ለዛውም በግርግር ውስጥ። ተሥፋ ቆርጦ ተመለሰ። በገባበት የፖለቲካ ትርምስምስ አገሩን ማየት አይችልም። እናቱን ፣ አባቱን አልቀበረም፤ ጓደኞቹ፣ ዘመዶቹ ሁሉ ባብዛኛው አልቀዋል።

ብጉርምስናው ዘመን ከፍቅረኛው ጋር ከንፈር የተሳሳመባት የወይራ ዛፍ ወይ ደርቃለች ወይም ደሞ በከርሰ-መቃብሯ ላይ እንደ ጥይት ባንዴ የተተኮሰ የዘመኑ ሃብታም ብዙም ህይወት የማይታይበት አሥር ፎቅ አቁሞበት ይሆናል። መገመት ብቻ ነው….ሁሉም ነገር ትዝታ ነው….. Read story in PDF: ምንሊክን በጎሪጥ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 3, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.