ማን ይናገር የነበረ….. የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ! (በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

           ዕድል አጋጣሚ፣ ለሰው ልጅ ስትመጣ፣
           መልካምና ክፉ፣ አላት ሁለት ጣጣ !!!
           (ከበደ ሚካኤል፣ “የዕውቀት ብልጭታ”፤)
የታኅሣሥ 1953ቱን (ዓ.ም) “ሥዒረ-መንግሥት” ዋዜማ፣ መባቻና ማግስት ያካተተ መጽሐፍ ታትሟል፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ፣ አቶ ብርሃኑ አስረስ ሲሆኑ፣ አሳታሚው ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ፣ ማን ይናገር የነበረ…..፣ የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ የሚሰኝ ሲሆን፣በ2005 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ ታትሟል፡፡  ይኼንን የሚያህል ቁምነገረኛ መጽሐፍ በ144.00 (አንድ መቶ አርባ አራት) ብር ገዝቶ ቁምነገር መዝረፍ ያጓጓል፡፡ ገጽ በገጽ ሲገልጡት ከ እሰከም ስለሌለው ነፍስን በሃሴት ያጭራል፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ አንበውት የማያልቅ ሃተታ የያዘ ድንቅ ድርሳን (Masterpiece) ነው፡፡ ድርሳኑን ደጋግሞ ማንበብ እውነትን የበለጠ ማወቅ ነው፡፡ “ድንቅ የሆነ ድርሳን” ነው ያልኩት ለማጋነን አይደለም፡፡ በእርግጥም፣ ውብ ነው! እጹብ ድንቅ ነው!….
ይኼው ልንገመግመው የመረጥነው መጽሐፍ እጅግ ከፍ ያለ የዋጋ የሚሰጠው፤ የነገረ-መረጃ (Intelegenece)፣ የወታደራዊ፣ የፖለቲካ፣ የሕግ፣ የታሪክ፣ የንግድ፣ የማህበራዊ ሳይንስና የግብረ-ሠናይ ይዘት ያለው ሥራ ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ በሀገራችን የነገረ-መረጃ (የስለላ-ነክነት) ያላቸው መጽሐፍት ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡ ያሉትም ትቂት መጽሐፍት ቢሆኑ የትርጉም ሥራዎች ናቸው፡፡ ለዚያውም ደግሞ የአቶ ማሞ ውድነህ ጥረቶች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡
አንደኛ፣ የደኅንነት (የመረጃ) መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎቹ በተከታታይ ሕይወታቸው በምስጢራዊ አኳኋን በማለፉና የሚያውቁትን ምስጢራዊ መረጃ ሊዘግቡት ባለመቻላቸው ነው፡፡ በጃንሆይ ዘመን የነበሩት የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሃላፊዎች በሙሉ በሰው እጅ አልፈዋል፡፡ አቶ መኮንን ሀብተ ወልድ ዋናው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሌ/ኮለኔል ወርቅነህ ገበየሁም ቢሆን ተታኩሶ ነው የሞተው፡፡ ኮ/ል ዳንኤል ደግሞ በሻለቃ ዮሐንስ አራት ኪሎ ቤተ-መንግሥት ውስጥ (ከነሰናይ ልኬ ጋር አንድ ቀን  ነው) የተገደለው፡፡ የደርግ  ዘመን፣ ለረጅም ጊዜያት የደኅንነትና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ኮ/ል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴም ቢሆን፣ ከ21 ዓመታት እስር በኋላ ሊለቀቅ ቀናት ሲቀሩት መሞቱ ተሰማ፡፡ ከርሱም ቀጥሎ ኃላፊነቱን የተቆናጠጠው “ተጋዳላይ” ክንፈ ገ/መድኅን በግንቦት 4/1993 ዓ.ም በጎልፍ ክለብ ተገደለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ክስተቶች ተደማምረው፣ የኢትዮጵያን የደህንነት መሥሪያ ቤት የሚመለከቱ መረጃዎች ከኃላፊዎቹ ጋር ተቀበሩ፡፡ የኃላፊዎቹንም ፍጻሜ ያዩት የመረጃ መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች “ጎመን በጤና” ብለው እንዲታቀቡ ጥላውን አጠላባቸው፡፡
Click here to read full story.

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 27, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.