ማን ነው የተዋረደው? (ይሄይስ አእምሮ)

ከጥቂት ሣምንታት ወዲህ በተለይ የኢትዮጵያን የወያኔ መንግሥት በሚቃወሙ የሚዲያ ማዕከላት ዘንድ ዋና መነጋገሪያ ሆኖ የሚገኘው በሳዑዲ የኢትዮጵያውያን መንገላታትና መሰቃየት እንዲሁም ከኢሰብኣዊነትም በወረደ ሁኔታ በግፍ መጨፍጨፍ ነው፡፡ ዜጎቻችን በአካፑልኮ ቤይ የመዝናኛ ሥፍራ ሲንሸራሸሩ ከርመው የመጡ ይመስል ይህ ምስል በኢትዮጵያው የወያኔ ሚዲያ በአስደሳች መልክ እየቀረበ ቢሆንም ትክክለኛውን መረጃ ከአማራጭ የዜና ምንጮች እንደወረደ እንደምንከታተለው ከሆነ ግን ከሀገርና ከሕዝብ ኅልውና አኳያ ነገሩ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ከአንድ ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንደሚጸነስ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ገጠመኝ ውስጥ የፈነጠቀው የሕዝብ አንድነት ግን በሌላ ወገን ተስፋችን እንዲያንሠራራ አድርጓል፡፡ ፈረንጆቹ “blessing in disguise” ወይም “mixed blessing” እንደሚሉት ይህ መጥፎ አጋጣሚ ሊረሳ የተቃረበውን የሕዝብ አንድነት በማደስ በመላው ዓለም የተበተነው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ቆሞ ድምፁን እንዲያሰማና ለጋራ ኅለውናው እንዲያለቅስ አስችሎታል፡፡ Read full story in PDF…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.