ሚድሮክ ፌዴሬሽኑን ሊምረው ነው (?)

ሚድሮክ ድርጅት ለሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን የ240 ሺህ ዶላር ልግስና መስጠቱ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑም በዚህ ገንዘብ መነሻ ዝግጅቱን በታላቁ የጆርጂያ ዶም ውስጥ ማድረጉ ይታወቃል። ከዝግጅቱ በፊት እና ከዝግጅቱ በኋላ እንደሰማነው ከሆነ ግን፤ የሁለቱም ወገን የህግ ሰዎች ተሰብስበው “ቢያንስ ግማሹን ገንዘብ ለመመለስ ተስማምተዋል” የሚለው ወሬ ተደጋግሞ እየተሰማ ነው።

አሁን በቅርቡ የሚሰማው ወሬ ደግሞ፤ እንዲመለስ የተባለውን ቀሪ 120 ሺህ ዶላር ጨርሶውኑ ለፌዴሬሽኑ ሊተውለት ነው የሚል ዜና እየተናፈሰ ነው። ፌዴሬሽኑ አትላንታ ላይ የሚያደርገው ዝግጅት ሁልጊዜም አትራፊ ሲያደርገው የቆየ ሲሆን፤ ከዋናው ምንጭ አልተረጋገጠም እንጂ እንደተባለው ከግማሹም አልፎ ሙሉውን 240 ሺህ ዶላር የሚያገኝ ከሆነ የገንዘብ አቅሙ ከፍ እንደሚል ይታመናል።

በዚህ የ28ኛው ዓመት ዝግጅት ፌዴሬሽኑ ከምግብ እና ደረቅ እቃ የድንኳን ኪራይ፤ እንዲሁም ሮዜታን ጨምሮ ከሌሎች ስፖንሰሮች ከመቶ ሺህ ብር በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል (በርግጥ ወጪም ይኖረዋል)። የመቶ ሺውን ገቢ ትተን… ከበር ላይ የሰባት ቀናት የስቴዲየም ክፍያ እና ከሙዚቃው ምሽት ሊገኝ የሚችለውን ገቢ ስናስብ የትየለሌ ይሆናል። እንዲያውም ከሚድሮክ ስጦታ የላቀ ገንዘብ ሊገኝበት እንደሚችል ሰፊ ግምት አለ።

በመጨረሻም የሂሳብ ስራው ሲሰላ ፌዴሬሽኑ በጥሩ የገንዘብ አቋም ላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ከዚህ በኋላ ወደ አትላንታ ተመልሶ እንደጆርጂያ ዶም አይነት ስቴዲየም ውስጥ ለማዘጋጀት ሌላ 5 እና አስር አመታትን ሊወስድ ይችላል። ስለሆነም አሁን ያለውን የገንዘብ አቅም ይዞ፤ በአመት አንዴ በሚገኝ ገቢ ላይ ብቻ ሳይወሰን ዘላቂ የሆነ ትርፍ የሚያገኝበትን መንገድ ቢቀይስ መልካም ነው። ለዚህም ከራሱ ጽ/ቤት ጀምሮ ሙሉ ጊዜ ሰጥተው፤ ድርጅቱን የበለጠ ትርፋማ ለማድረግ የሚሰሩ ፕሮፌሽናሎችን በመቅጠር የወደፊት ስራውን መተለም ይኖርበታል… በሚል መልካም አስተያየት ዘገባችንን እናበቃለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 18, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.