ሚኒስትሯ ግብረሰዶማዊነትን ደግፈዋል በሚል የተሰራጨውን መረጃ አስተባበሉ

የኢትዮጵያ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ የኡጋንዳ መንግስት በግብረሰዶማውያን ላይ ያወጣውን ሕግ እንደተቃወሙ ተደርጎ በግል የቲውተር ገፃቸው ላይ የሰፈረውን መረጃ አላውቀውም ሲሉ በሚኒስትር መ/ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኩል አስተባበሉ።
ሚኒስትሯ በግል የቲውተር ገፃቸው አሰራጩት በተባለው አጭር መልዕክት ላይ የኡጋንዳ መንግስት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ የተሰማሩ ዜጎችን እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ቅጣት መቅጣቱን መቃወማቸውንና በግብረሰዶማዊነት ላይ መንግስት ሕግ የማውጣት ኃላፊነት እንደሌለበት የሚጠቁም መልዕክት እንዳስተላለፉ ተደርጎ ቀርቧል።

ሚኒስትሯ መልዕክቱን ያስተላለፉት የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በግብረሰዶማዊነት ላይ ጠንካራ ሕግ በፊርማቸው ማፅደቃቸውን ተከትሎ ነው። የሚኒስትሯም አቋም በኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ዓለም አቀፍ ውግዘት መቀላቀላቸውን የሚያመለክት እንደሆነም ተገልጿል። የሚኒስትሯን አቋም የኡጋንዳ የግብረሰዶማውየን መብት ታጋይ ፍራንክ ሙጊሻ አወድሰዋል።
የወ/ሮ ዘነቡ የግል አስተያየት በቲውተር ገፃቸው ከወጣ በኋላ የግብረሰዶማውያን መብት ታጋዩ በቀጣይ ሕጉን ለመቃወም የሚደረገውን ትግል እንደሚያግዝ አያይዘው ተናግረዋል። ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ የግብረሰዶማውያን መብት ተቆርቋሪ የሚኒስትሯ አስተያየትን ጠቃሚ በማለት አወድሰዋል። ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮችም የወ/ሮ ዘነቡን ፈር መከተል ያለባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

የደቡብ አፍሪካው የግብረሰዶማውያኑ መብት ተከራካሪ ሜላኒ ናትሐን ጨምረው እንደገለፁት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የተከበረበት የደቡብ አፍሪካ መሪ ጃኮብ ዙማ ዝምታን በመረጡበት ሁኔታ ኢትዮጵያዊቷ ሚኒስትር በሕጉ ላይ በድፍረት መናገራቸውን በአድናቆት ገልፀውትም ነበር።

ኢትዮጵያ ጠንካራ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሕግ ያላት ሲሆን፤ በዚህ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ ሰው እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ መሆኑንም ይታወቃል።

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የፀረ-ግብረሰዶማውየንን ሕግ በፊርማቸው ካፀደቁ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እየገጠማቸው ነው። ፕሬዝዳንቱን ካወገዙት መካከል የደቡብ አፍሪካው የኖቤል ሽልማት አሸናፊው ቄስ ዴዝሞን ቱቱ ይገኙበታል። ቄስ ቱቱ የኡጋንዳውን የፀረ-ግብረሰዶማዊ ሕግ ከናዚ እና ከአፓርታይድ ድርጊት ጋር ማነፃፀራቸውም እየተዘገበ ነው።

የኡጋንዳው የፀረ-ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሕግ በድርጊቱ የተሳተፉ ሰዎችን ዕድሜ ልክ ከመቅጣት ባሻገር ሁኔታውን እያወቁ በዝምታ የሚያልፉትን ጭምር በወንጀል የሚያስጠይቅ ነው።
ሕጉ በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ማድረግንም ሆነ በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መፈፀም፣ ማበረታታትና እያወቁ ዝም ማለትን እንዲሁም በጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉ ከሆነም 14 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ያስቀጣል። ሕጉ ከወጣም በኋላ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሕጉ ኋላ ቀር መሆኑን በመጥቀስ አምርረው ተቃውመውታል። በቀጣይ ኡጋንዳ ከአሜሪካ የምታገኘው 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መውደቁ እየተነገረ ነው። ኡጋንዳ የፀረ-ተመሳሳይ ጾታ ሕግ ብታወጣም በሀገሪቱ ድርጊቱ ከተስፋፋባቸው የአፍሪካ አገሮች መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

W/ro Zenebu Tadesse

W/ro Zenebu Tadesse


ጉዳዩን በተመለከተ የሴቶች የህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ለሰንደቅ እንደተናገሩት ያልታወቁ ሰዎች የሚኒስትር ዘነቡን የቲውተር ገፅ የሚስጥር ቁልፋቸው (Passwords) በመስበር መረጃው መልቀቃቸው አስታውቋል።

የሚኒስትር መስሪያቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብይ ኤፍሬም መረጃው የተሰራጨው የሚኒስትሯ የተለያዩ የፖሊሲ ጉዳዮችንና ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በግላቸው በሚያሰራጩበት የቲውተር ገፃቸው የተለጠፈውን መረጃ ለማጣራት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጥረት ሲያደርግ መዋሉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በሚኒስትሯ ስም የተሰራጨው መረጃ የሚኒስትሯንም ሆነ የመንግስትን አቋም የማይወክል፣ መሆኑን የቲውተር ገፁም ለጊዜው መታገዱን አመልክቷል።

Source: Sendek

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 26, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to ሚኒስትሯ ግብረሰዶማዊነትን ደግፈዋል በሚል የተሰራጨውን መረጃ አስተባበሉ

 1. AleQa Biru

  February 26, 2014 at 6:30 PM

  በጣም ይገርማል!!
  እኛ አፍሪካውያን ስንባል መተባበር የሌለብን ቦታ ላይ ስንተባበር እንገኛለን:: ለምሳሌ የሰብአዊ መብቶችን ለመጨቆን እያንዳንዱ አፍሪካዊ በአንድ ድምጽ የተስማማ ይመስላል:: በእያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሕብረተሰቡ የአናሳዎችን (ለምሳሌ ሆሞዎችን / ግብረ-ሰዶማዊያንን) ሰብአዊ መብት እንዲጨቆን/እንዲረገጥ ይስማማል:: ሰብአዊ መብቶች ግን በአብላጫ ድምጽ የሚወሰኑ አይደሉም:: ለዚህ ነው መተባበር የሌለብን ላይ ስንተባበር እንገኛለን ያልኩት::

  በተቃራኒው ደግሞ መተባበር ያለብን ጉዳይ ላይ ስንፍረከረክ እና ስንውሸለሸል እንታያለን:: በአብዛኛው የአፍሪካ መንግስታት አምባገነኖች ናቸው:: የተባበረ የሕዝብ ድምጽ ቢኖረን ኖሮ አምባገነኖቻችን ውለው ባላደሩ ነበር::

  በመጨረሻም መናገር የምፈልገው መፍረድ የሚችለው እግዚያብሔር ብቻ መሆኑን ነው እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ:: ምክንያቱም አትፍረድ ይፈረድብሐል ተብሏልና (ሉቃስ 6:37)

 2. ሐዱሽ

  March 1, 2014 at 6:01 AM

  የወ/ሮ ዘነቡ አሉት እየተባለ ያለውን ለማመኑ በጣም አስቸጋሪ ስለ ሆነ ለበለጉዳዩዋ እንተዎው የሚገርመው ግን እኛ አፍሪካውያን ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀኝ አገዛዝ ወጣን ብለን ለእድገታችን ደፋ ቀና በምንልበት ወሳኝ መድረክ መድረሳችን ይታወቃል። ይህ የማይዋጥላቸው አካላት በግልፅም ሆነ በስውር ከመዳፋቸው እንዳንወጣ የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ እየታወቀ ኡደንዳ ባወጣቸው የፀረ ግብረ-ሰዶም ሕግ የደቡብ አፍሪካንና የሌሎች አፍሪካ ሃገራት ሙሁራንና ሌሎች መቃወማቸው ሚያሳዝን ነው። ግብረ ሰዶም በአፍሪካ መስፋፋት ማለት የአፍሪካውያን ባህልና ሃይማኖት በባዕድ ባህልና ወግ እየተወረረ ዳግም ቀኝ ግዛት ማለት እንደ ሆነ እያወቁ መደገፍ ከተላላኪነት ያለፈ ትርጉም የለውም። በሃገራችን ኢትዮጵያም ይህ ለማስፋፋት የሚፈልግ ግለ ሰብ ይሁን የመንግስት አካል ለግሉ ሲል ህዝብና ሃገር እንደ ሸጠ እኛ ኢትዮጵያውን እንገነዘባለን። ግብረ-ሰዶም ባህላችንና ሃይማኖታችን የማይፈቅደው አፀያፊ ስለ ሆነ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሊታገው ይገባል። ተመሳሳይ ፆታ በገብቻ መፍቀድ እንደ ስልጣኔ ሳይሆን እንስሳነት ነው። ቀኝ ግዛት ያልሰለቸው ካለ ለራሱ በሃገሩ ይገዛ እንጂ አብራችሁ ከኔ ጋር ተገዙ እያሉ የሚያጫፍሩ ጭፈራቸው ቢያቆሙ ይሻላል።

 3. AleQa Biru

  March 1, 2014 at 2:18 PM

  ሐዱሽ:

  በመጀመሪያ በኡጋንዳ የወጣው ህግ ስለ ተመሳሳይ ጾታዎች ጋብቻ አይደለም:: እሱማ ሌላ ደረጃ ላይ የሚደረግ ክርክር ነው:: ይህኛው ግን ስለማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ነው:: ሁለቱ ጉዳዮች በጣም የተለያዩ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል:: በብዙ የምእራብ አገሮች የግብረ-ሰዶማዊያን (ሆሞዎች)ራሳቸውን የመሆን መብት የተጠበቀ ነው:: ይህም ማለት ማንኛውም ሰው እንደሚያደረገው ሁሉ የፈለጉትን የማፍቀር እና ፍቅራቸውን የመግለጽ (በመሳሳም, በመተቃቀፍ ወዘተ) መብት አላቸው:: ነገር ግን የመጋባት መብት ግን ያላቸው ጥቂት በሚባሉ አገሮች ብቻ ነው::

  እንደ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ በመሳሰሉ አገሮች ግን እንኳን ስለጋብቻ ቀርቶ ስማቸውን ለመጥራት እንኳ አልተቻለም:: ስለዚህ ስለ ጋብቻ ያለከው ገና ያልደረስንበትን ችግር ነው::

  እኛ አፍሪካዊያን ስለ ግብረ-ሰዶማዊያን በተመለከተ መወያየት ያለብን የሚከተሉትን ይመስለኛል::

  1. ግብረ-ሰዶማዊያን ሰዎች ናቸው ወይስ አይደሉም?
  2. ግብረ-ሰዶማዊነት ምንድነው? ቅንጦት, በሽታ,ተፈጥሮ ውይስ ሌላ?

  ለመጀመሪያው ጥያቄ መልሳችን “ግብረ-ሰዶማዊያን ሰዎች ናቸው” ከሆነ (የሁለተኛው ጥያቄ መልስ ምንም ይሁን ምን) የግብረ-ሰዶማዊያን መብቶች እንደማንኛውም የሰው ልጅ ምብቶች ማክበር ይኖርብናል:: የነሱን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር የግድ ከክርስትና ወይንም እስልምና ወይንም ሌላ ሀይማኖታችን ጋር መጋጨት አያስፈልግንም:: ከሀይማኖታችን አኳያ ድርጊታቸው በእግዚአብሔር ያልተፈቀድ መሆኑን ምንም ሳንሸማቀቅ መናገር መብታችን ነው:: ነገር ግን በድርጊታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት የሚጠየቁት እነሱ እንጂ እኛ አይደለንም:: እግዚአብሔር የከለከለውን ድርጊት ስለፈጸሙ ፍርድ የሚያገኙትም ከፈጣሪያቸው ክእግዚአብሔር እንጂ ከሰው ልጅ ዘንድ ሊሆን አይገባም::
  ባጭሩ እኛን አይመለከተንም:: እኛን የሚመለከተን ካልፍላጎታችን እንደነሱ ሊያደርጉን ከቃጣቸው ብቻ ነው:: ይህን የሚያደርጉ ከሆነ ደግሞ የእኛን መብት የሚጋፉ ስለሚሆን በአለው ሕግ መቀጣት ይችላሉ::

  እኛም ራሳችንን የመሆን መብታችን ይኑረን እነሱም ይኑራቸው ባይ ነኝ::