“ሙሰኞቹ” ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ ሌሎችም ታሰሩ!

(EMF) ከመለስ ዜናዊ ጀርባ ይቀመጥ የነበረው የህወሃት አባል፤ አስመላሽ ወልደማርያም ዛሬ ከቀድሞ የጉምሩክ ዳይረክተር አቶ መላኩ ፈንታ ጋር ዛሬ 2ኛ የፌዴራል ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ከነሱም ጋር አቶ እሸቱ፣ አቶ ማርክነህ፣ አቶ ከተማ፣ አቶ ስማቸው እና አቶ ፍቅሩ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የአቃቤ ህግ ክስ እንደሚያስረዳው “ግለሰቦቹ ህግ እና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሌሎችን ቢዝነስ በድለዋል” የሚል ይዘት ያለው ነው።
corruption
በሌላ በኩል ደግሞ የህወሃት አባል እና የጉምሩክ ም/ል ዳይረክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ በተመሳሳይ መልኩ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ችሎት ቀርበው ነበር። ፖሊስ በጠቅላላ ተከሳሾች ላይ፤ ለተጨማሪ መረጃ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። ሆኖም ተከሳሾች ቢሮ እና ቤታችን ተበርብሮ መረጃ ስለተወሰደ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠት የለበትም፤” ሲሉ ተቃውመዋል። በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ መረጃውን እስከነገ ጨርሶ ነገ እንደገና እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።

“ተከሳሾች ከሃይማኖት አባቶች፣ ከጠበቆች እና ከቤተሰባችን ጋር እንዳንገናኝ ተደርጓል። ህገ መንግስታዊ መብታችን ተገፏል።” በማለት ቅሬታ አሰምተዋል። ከዳር ሆኖ ሁኔታውን ለሚታዘብ ሰው፤ የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ ትንሽ ፈገግ ሊያሰኝ ይችላል። እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዕዮት አለሙና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ሃሳባቸውን በነጻ ስለገለጹ ብቻ “አሸባሪዎች” ተብለው መብታቸው ተገፎ ሲሰቃዩ በሞቀ ቤታቸው ተንደላቀው ተኝተው ነበር። አሁን ግን በሙስና ወንጀል ተከሰው ውሎ እና አዳራቸው እስር ቤት ሆኗል።

በቅርቡ እስክንድር ከቃሊቲ በላከው የእንግሊዘኛ ደብዳቤ ላይ የጻፈውን እዚህ ላይ ማስታወሱ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። “አሳሪዎቼ በሞቀ አልጋቸው ውስጥ ከሚስቶቻቸው ጎን በቤታቸው ይተኛሉ። እኔም ቅማልን ብቸኛ ጓደኛዬ አድርጌ፤ በእስር ቤት ውስጥ ለሊቱን አሳልፋለሁ – የህሊና ሰላም ግን አለኝ።” ብሎ ነበር። እነዚህ ሰዎች… የእስክንድር ነጋን አባባል ሊጋሩት ይችላሉ። ሆኖም ህሊናቸው ነጻ ስላልሆነ፤ ስቃያቸው የበዛ ነው። ትላንት በሌላው ሲዛበቱ እና ሲስቁ፤ በሙስና ወንጀል ሲራቀቁና ሲሰርቁ ነበርና ዛሬ የህሊና ሰላም የላቸውም። ወደፊት በህግ ከተፈረደባቸው ደግሞ፤ የእስር ቤት ቅማል ገላቸውን ብቻ ሳይሆን ህሊናቸውንም ይበላዋል። ለሁሉም ግን የፍርድ ሂደቱን ተመልክተን ወደፊት የምንለው ይሆናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የናዝሬቱ ጉምሩክ ሃላፊ ተመስገን ጉልላት ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በጋምቤላ በኩል አድርጎ ሊጠፋ ሲል ተይዟል። የጋምቤላ ጉምሩክ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋም የናዝሬቱን ሃላፊ በመርዳቱ አብሮ ታስሯል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 13, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to “ሙሰኞቹ” ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ ሌሎችም ታሰሩ!

 1. ፕሬስ

  May 14, 2013 at 4:15 AM

  የኢትዮጵያ ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተቋቋመው ህብረተሰብን ሊያስተምርና ሊያነቃ ዘራፊዎችን ወደ ህግ እያመጣ ሊያስቀጣ፣ ሙስናን ሊያጠብ የሚችል ሲስተም ሊፈጥርነበር ነገር ግን መጀመሪያውንም ሲቋቋም በውነትም እነዙህን ነገሮች ለማድረግ ሳይሆን ለማስመሰል በተለይም ደሞ የፖለቲካ ተቃዋሚ የሆኑትን፣ ጀርባቸው እየተጠና የሚከሰሱበት መስሪያ ቤት ሆኖ ያገለግላል። ዝርፊያ መንግስትን ካልተቃወሙ ብዙም ወንጀል ኣይደልም ኢትዮጵያ ውስጥ።
  ያ ሁኑ ዘማቻስ ይሄው እንደሆነ ማን ያውቃል?

 2. alemie bukaya

  May 17, 2013 at 5:31 PM

  ay gize andande lehulum gize alew sibal sisema bizum simet aysetegnim neber. ahun gin betinishum bihon kelben sibotal. tikurete be ato asmelash lay new ATOW yihich asteyayete tidersowet wois atidersewot alawikim. tiz yilwot yihon yezare amet akababi. para olompic zena sisera min endalugn. ersowe yih gize yemayalf meslowot yebedeluachewun siportegnoch bedel media lay endalawilew endet endasferarugn. enes min biyewot neber astawesu. endefokerubign balhonim ageren endilek kemikinyatoche mehal andu honewal. gize gin feraj new. lehulum gizialew bilual selemon.