መንግስት… የአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት አመት እንዳይከበር የፈለገ ይመስላል

ከሁለት ሳምንት በኋላ፣ ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. አጼ ምኒልክ ካረፉ 100 አመት ይሆናቸዋል። ይህንን 100ኛ አመት በክብር ለማሰብ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በጃንሜዳ የፎቶ ኤግዚብሽን እና የፓናል ውይይት አዘጋጅቶ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም የአዲስ አበባ ከንቲባ በሰጠው የደብዳቤ ምላሽ “ቦታው ለጥበቃ አመቺ አይደለም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ጃንሜዳ በግንብ የታጠረ ትልቅ ሜዳ ነው። ዙሪያውን የታጠረ በመሆኑ ለጥበቃ እጅግ አመቺ ስፍራ መሆኑ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ደብዳቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ደብዳቤ

ከዚህ ደብዳቤ መንፈስ በግልጽ የምንረዳው አንድ ነገር ቢኖር፤ መንግስት የአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት አመት እንዲከበር የማይፈልግ መሆኑን ነው። አጼ ምኒልክ በኢትዮጵያ ዘመናዊ አስተዳደር እንዲመጣ፣ ነጻነቷን የጠበቀች አገር እንድትሆን፣ ዘመናዊ የሆኑ ነገሮች እንዲጀመሩ፣ ህዝቡ እንዲማር… ከምንም በላይ የዛሬዋ ኢትዮጵያ በአንድነት እንድትቆይ ያደረጉ መሪ መሆናቸው ይታወቃል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to መንግስት… የአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት አመት እንዳይከበር የፈለገ ይመስላል

 1. በለው!

  December 4, 2013 at 6:31 PM

  ”በአንድ ወቅት የቀዳማዊ ኀይለስላሴን ሙት ቀን ለመዘከርና ለእራሳቸውም ማስታወሻ የሚሆን መታሰቢያ ሐውልት እንዲቆም ጉዳዩ የሚመለከታቸውና ቤተሰቦቻቸው እኛ የሞቱ ጠ/ሚርን በጠየቁ ግዜ…እንዲህ ብለው መልስ ሠጡ፡፡ (፩)”አፄው ከሞቱ ብዙ ግዜአቸው ነው የምትጠሯቸውም ሰዎች ግራ ይጋባሉ… * የሚሰራው ሀውልት ግን….!
  (፪)አጼው ሲሞቱ በሥልጣን ላይ አልነበሩም ከሥልጣን ወርደው ነው የሞቱት፡
  (፫)ሐውልት እንዲሰራበት ተጤቀው ክልልና ቦታው የሌላ ብሔር ስለሆነ ሌሎችን ሊያስቀይም ይችላል፡ለመታሰቢያነት ግን ትንሽ ነገር ያለ ፎቶ ቢቆም ክፋት የለው”
  ***********
  አሃ! ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ በቁማቸው በነሐስ ሐውልት ያሰሩት ክልሉ የእሳቸው ነው።ታጋይ ህወአት እና የአሜሪካ ምሁር ስለሆኑ ነው። ብሔር ብሔረሰብ መነገጃነቱ ይህ ነው።”ተጨቁነህ ማንነትህ ሳይታወቅ እና በማኒፌስቶ የፈጠርንህ ሲባል የሚፈነጥዘው ለዚህ ነው።
  *ህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስቱ)አንድ ገጽ ተኩል ሥልጣን አስተቀለላቸው ተጠቅላይ መልስ ዜናዊ እነዴት በዘጠኑም ክልል ለመቀበር ቻሉ። ታጋይ አይሞትም!ምንአልባት መለስን የገደሏቸው ከሥልጣን ሳይወርዱ ሞቱ ብለው በሀውልት ሊያንበሸብሻቸው ነው ማለት ነው።እውነትም እራዕዩን እናስፈጽማለን!?ፈፀሙባቸው በለው ወይ ጥጋብ!
  ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ የማን ናት!?”የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ” አለ
  **ለጠላታችን ግራዘያኒ መታሰቢያ ሐውልት መቆም ተቃውሞ ካልተወጣባት **ወገን ላሠረ፣ ለገረፈ፣ለደፈረ፣ሰደቅን ላንቋሸሸ፣ሉዓላዊነትን ላዋረደ፣ዓረብ ኢትዮጵያዊው ሕዝባዊ ተቃውሞ ማሰማት ከተነፈገ ከታሠረ ከተደበደበ፤ ኢትዮጵያ አለችን?
  *ግለሰቦች የራሳቸውን ሥምን ዝና ሐውልት በእየሙዚየሙ ከሰቀሉ፤ ሳይሞቱ ምስላቸውን ቀርጸው ማስመለክ ከቻሉ በእርግጥም ህወአት ብሔር ብሔረሰቦችን የቁም ከብት አድርጓቸዋል። በሬ ከአራጁ ይውላል ማለት አደለም!
  **ለመሆኑ ይህ የቀድሞ መሪዎቻችሁን አታስታውሱ ታሪክ ተፅፏል፤ ሀገር ፈርሶ ክልል ተገንብቷል ወጣቱ ሁሉ የተደቀለው በህወአት ነው ማለት ይሆን? አዲሲቷ ሀገር በመፈቃቀርና በመከባባር በአንድ ፖለቲካ ጥላ ሥር ተንበርክኮ የህወአትሻቢያ አሽከር መሆን። የ፻ዓመት ታሪክ፣የሚሊኒየም ክብረ በዓልና የሚሊኒየም ግብ(ጉድጓድ)
  **ለህወአትሻቢያ መስቀል አደባባይ ለብሔር ብሔረሰብ ጃንሜዳ ተብሎ የተወሰነው ተሻረ ማለት ነው።ይህንን የሚሰራው የህወአት ግራ ክንፍ ሙስና ሻንጣ ተሸካሚው ኦነግና ኦብነግ ብአዴን(አማራ መሳይ ዲቃሎች ማህበር)መሆን አለባቸው። ይቺን ካልተቃወሙ ይጋለጣሉ! ይባረራሉ! ይታሠራሉ! ይገደላሉ!አድርባይ አሉ ወ/ሮ አዜብ ይህ በእነ እነድሪያስ እሸቴ(ጣረሞት) ሆድ-አደር ምሁር ተብዬዎች የተቀመመ መርዝ ነው። በትግራይ ተወላጆች ሚሰራ ብቻ አደለም። ሸዋ እጅህን አላግባብ አንድ ቦታ መቀሰርህን አቁም ጠላትህ በሁሉም ቤተሰብና ክልል ብሔር ውስጥ ነው። እራስህን ፈትሽ!ንቃ ተደራጅ!
  “የፎቶግራፍ ኢግዚቪሽንና የፓናል ውይይት ለማካሔድ የተመረጠው ቦታ ጃንሜዳ ውስጥ ለፀጥታ ትበቃ አመቺ ባለመሆኑ የተጠየቀውን ዕውቅና ጥያቄ ዕውቅና ለመስጠት የምንቸገር መሆናችንን እንገልፃለን። ከሰላምታ ጋር!
  **ይህ ቃል ከህወአት ቋንቋ ወደ ብሔር ብሔረሰቦችና ሲተረጎምና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሲተላላፍ: _መረጃና ብጥብጥ አገልግሎት፣
  _ለህወአት ፖሊስ ቡድን ኮሚሽን፣
  _ለአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ወንጀል አቀነባባሪ ፖሊስ ንዑስ ኮሜቴ ከምስጋና ጋር!
  “ዝግጅቱ እምዬ ምንይልክን አስታኮ ቦንብ ለመቅበር፤ አዘጋጆችን ለማሰር፤ ተሳታፊውን ለማሸበር ዘግጅቱ ብዙ ወጪ አለው ጥቅሙ ይህን ያህል ፊልም ሊያሰራ ብቁ አደለምና ተረጋጉ፣ እናንተም አዘጋጆች የእኛን ጉልበት የሚመጥን ብጥብጥና ሁከት ሊፈጥር የሚያስችል ብዙ አድር-ባይ፣ ካድሬ፣ ሌቦችን፣ ሊያሳትፍ የሚችል ደመቅ ያለ ትርፋማ ሆነ ዝግጅት አዘጋጁ በማለት ተከለከለ የሚል ትርጓሜ አለው። ዘመኑ ሥራ መክፈት ድህነትን ማታገል አደለም!?
  **ጎበዝ የዚህ ዘመን ባንዳ ከመቼውም በበለጠ በቂ እርምጃ ያለ ምህረት ሊወሰድበት ይገባል።ኢትዮጵያ መጨረሻው መስቀልኛ መንገድ ላይ ናት እናልፋለን ወይም እንጠፋለን።እምዬ ምንይልክ በመላው ጥቁር ሕዝብ ልብ ውስጥ ይገኛሉ ይኖራሉ ይከበራሉ!። አሁን የሀገር ሉዓላዊነት ፣ዜግነት፣ የትውልድ ምንነት የመከነበትና የባከነበት፣ሰንደቅ የተዋረደበት የጠፋበት ወቅት ላይ ነንና!ሀገር ሲድን ታሪክ ይተርፋል!!ቅድሚያ ሀገርን ለማዳን ሙሰኛን፣ አድርባይ፣ አስመሳይ፣ሆድ-አደርን፣ ሌባን፣ ከአካባቢህ አጥራ!ሸዋ ተበላህ በላው። ሠላም ለሁሉም! ስለማንነታቸው የሚያውቁ ሁሉ ስለ ታሪክና ሀገር ይጨነቃሉ!!አለበለዚያ ተናጋሪ እንስሳ ሆኖ እየበሉ ለመኖር ሳይሆን ለመብላት መኖር ይባላል በለው!። ይታሰብበት በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ!

 2. tersit yemane

  December 9, 2013 at 3:40 AM

  deros yetaliyan ashker aydel ende tplf this shows u are really on the side of fascist italy …shame on u tplf a big shame. God knows u wont stay long so the judgment of God is near and HE will show u HIS hand soon cause u are abusing ethiopian ppl and ethiopian history !!!! peace to my beloved ppl who are God fearing and are powerful cause of their belive.