ሊቢያ – ትሪፖሊ በከፋ ጦርነት ላይ: ከውጭ የተገዙ ወታደሮች ህዝቡን በአውሮፕላን ደበደቡ

EMF- ነጻነትን የናፈቀው የሊቢያ ሀዝብ በኮሎኔል ጋዳፊ ታማኞች በተከታታ ቢጨፈጨፍም: ግድያው በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን የነጻነት አብዮት ሊያቆመው አልቻለም:: በተለይ የትላንቱ እና የዛሬው የህዝብ ቁጣ በታሪክ ትልቅ ስፍራ ይይዛል:: በሊቢያ የጀኖሳይድ (የጅምላ ግድያ ) ወንጀል እየተፈጸመ ነው ሲሉ ምእራባውያን እየተናገሩ ነው:: እንደ ቢቢሲ ዘጋባ በጉዳዩ የተባበሩ መንግስታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገባም ግፊት እየተደረገ ይገኛል::

ሰልፉን በሃይል ለማስቆም ወታደሮቹ ቢታዘዙም: ወታደሮቹ ወገናችንን አንገድልም: አልታዘዝም – በማለታቸው ኮሎኔል ጋዳፊ ከውጭ ቅጥረኞችን በማስገባት በዛሬው እለት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ በተዋጊ ጀቶች መድፍና ጥይት ሲያወርድ ውሏል:: የጋዳፊ ታማኝ የነበሩት በተበበሩት መንግስታት የሊቢያ ዲፕሎማት: ኢብራሂም ዳባሺ ጋዳፊ ከስልጣን እንዲወርዱ እና በዘር ማጥፋት ወንጀል አለም አቀፍ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ጠይቀዋል::

በትላንትናው እለት ኮሎኔል ጋዳፊ በብሄራዊ ቴሌቭዝን ለህዝቡ ንግግር ያደርጋል ተብሉ ሲጠበቅ ንግግር ያደረገው ልጁ ነበር:: የጋዳፊ ልጅ – ሊቢያ ግብጽ እና ቱኒዝያ አይደለችም:: አንድ ሰው እና አንድ ጥይት እስኪቀር ድረስ እንጨፈጭፋችኋልን ሲል ህዝቡን አስጠንቅቆ ነበር::

ሮይተርስ የዜና ምንጭ እና የንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሎኔል ጋዳፊ ወደ ቬኒዙዌላ ማቅናታቸውን ይፋ አድርገዋል::

በርካታ የሀገሪቱ ከተሞች በተቃዋሚ ሰልፈኞች እጅ ወድቀዋል:: በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት ልኡክን ጨምሮ የጋዳፊ ታማኝ ዲፕሎማቶች ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው እየለቀቁ ነው:: ትሪፖሊ ላይ ህዝቡን እንዲጨፈጭፉ ወደ ትሪፖሊ የተላኩ ሁለት ኮሎኔሎች ትእዛዙን በመቃወም ተዋጊ ጀቶችን ይዘው ወደ ማልታ አምልጠዋል::

የጋዳፊ ልጅ ዛሬ ማምሻውን ማናቸውንም የመገናኛ ብዙሃን: የቴሌፎን መስመሮች: እና ኢንተርኔት እንዲቆረጥ አድርጓል::

በተለይ ከውጭ ተገዝተው የመጡት ቅጥረኞች ባደረሱት የቦንብ ውርጅብኝ የተበሳጩ የሊቢያ ወታደሮች: ፖሊሱ: የእምነት አባቶች እና የሰራተኛ ማህበራት ሰልፈኞቹን እየተቀላቀሉ ነው::

ከብዙ መስዋእትነት በኋላ ሊቢያ የነጻነት ጎዳና ጫፍ ላይ ደርሳለች: ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ናት: የኢትዮጵያም ነጻነት ሩቅ አይደለም: …

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 21, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.