ለወገን ደራሽ ወገን – ሕዝባዊ ስብሰባ በቬጋስ

በላስ ቬጋስ በነሐሴ 23/2011 ለኢትዮጵያ ወቅታዊ የረሃብ አደጋ ለመድረስና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ሕዝባዊ ስብሰባ ተጠርቷል። የስብሰባው ዓላማ በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵአዊ የድርቁን አደጋ አስመልክቶ በቂ ግንዛቤ አስገኝቶ የበኩሉን አስተዋጽኡ እንዲያደርግና ከዚህ የተገኘው ገንዘብ ነጻና ገለልተኛ ለሆኑ የረድዔት ድርጅቶች ተሰጥቶ ለሕዝቡ እንዲደርስ የአቅማችንን ለማድረግ ሲሆን በወቅቱም በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በፖለቲካ ወገንተኝነት የእርዳታ ገንዘብም ሆነ እህል ይቃወሙኛል ላላቸው እየከለከለ የሚያደርሰውን በደል አንስቶ በመወያየት ለጋሾች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለሕዝቡ መድረስ እንዲችሉ የበኩላችንን ትሪ ማድረስና ሕዝቡ በወገኑ ላይ በስርዓቱ የሚፈጸመው በደል በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ ነው። በስፍራው በወቅታዊ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል ከሚባሉ ሌላው ዋነኛ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ የመጣው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ላይ ነው። አቶ ኦባንግ ሜቶ የስብሰባው ተጋባዥ የዕለቱ እንግዳ ናቸው። ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መሪ ቃል በቬጋስና በአካባቢው የሚኖሩ ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በዚህ ስብሰባ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 11, 2011. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.