ለኢድ በአል… የአዲሳባ ስቴዲየም ለ20 ሺ ሰዎች ብቻ ክፍት ሊሆን ነው

EMF – ባለፈው አመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሞተው ሳለ፤ “አልሞቱም” እየተባለ፤ በውሸት ሽንገላ ሳምንታት መቆጠራቸው ይታወሳል። የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ካልሆነበት ምክንያት አንደኛው፤ ወቅቱ የረመዳን ጊዜ በመሆኑና ሙስሊሙ ህብረተሰብ ደግሞ ጾም በሰፊው በመያዙ ነበር። በዚያ ላይ አርብ አርብ በሚደረገው የጁምዓ ሰልፍ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ሃዘኑን ይግለጽ ወይም “እንኳን ሞቱ” ይበል… ብቻ ምን ሊባል ወይም ሊፈጠር እንደሚችል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር ያለፈው አመት ረመዳን ያለፈው። እንዲያውም የረመዳን ጾም አልቆ የኢድ እለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በታሪኩ ለማንም አድርጎት የማያውቀውን ቀኑን ሙሉ የፈጀ የኢድ በአል ዝግጅት በቀጥታ ሲያሰራጭ ውሎ አመሸ። ይሄ ሁሉ ታዲያ ህዝበ ሙስሊሙን ለመለማመጥ ጭምር ያደረገው ጥረት መሆኑ ግልጽ ነው። አሁን ደግሞ በአመቱ ምንድን ሊፈጠር እንደሚችል ባናውቅም፤ ለኢድ በአል የእምነቱ ተከታዮች የራሳቸውን ዝግጅት ሲያደርጉ፤ ኢህአዴግ ደግሞ በበኩሉ ሰራዊቱን ለማሰማራት ሽር ጉድ እያለ ነው። ለጥንቃቄም ሲባል በአሉ በሚዘጋጅበት ስቴዲየም ውስጥ 20 ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ እንዲገቡ መታቀዱን የ”ድምጻችን ይሰማ” ዘገባ አመልክቷል። (ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

We are asking our Right, but they are killing us!

We are asking our Right, but they are killing us!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.