ለነገው ጨዋታ ዛሬ ሰልፍ ተጀመረ (አራቱም ዳኞች ግብጻውያን ናቸው)

(EMF) ነገ ከሰዓት በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፤ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ወሳኝ ግጥሚያ ያደርጋሉ። ይህንን ጨዋታ ለማየት የኢትዮጵያ ቡድን ደጋፊዎች፤ ገና ካሁኑ ስቴዲየሙን አጥለቅልቀውታል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ፎቶ ግራፍም የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከደቡብ አፍሪካ ጋር ባደረገችው ጨዋታ፤ 1-1 ስለወጣች፤ የነገውን ጨዋታ 0-0 ብትወጣ ወይም ብታሸንፍ፤ አስሩ ውስጥ የመግባት እድሏ ሰፊ ብቻ ሳይሆን የተረጋገጠ ሊሆን ይችላል። ሆኖም የነገው ጨዋታ በአንድ ለየት ባለ ክስተት የተሞላ ይመስላል። ጨዋታውን የሚመሩት አራቱም ዳኞች፤ (ዋናው ዳኛ Mohamed FAROUK፣ 1ኛ መስመር ዳኛ Ayman DEGAISH፣ 2ኛ መስመር ዳኛ እንዲሁም 4ኛው ውዝግብ ከተነሳ የሚዳኘው የውጭ ዳኛ Mahmoud AHMED) ሁሉም ከግብጽ ናቸው።

ይህ የምታዩት ሰልፍ ስቴዲየም ለመግባት ሳይሆን፤ በስታዲየም ዙሪያ አድረው ነገ ቲኬት ለማግኘት የተሰልፉ ናቸው።

ይህ የምታዩት ሰልፍ ስቴዲየም ለመግባት ሳይሆን፤ በስታዲየም ዙሪያ አድረው ነገ ቲኬት ለማግኘት የተሰልፉ ናቸው።

ሁሉም ዳኞች ከግብጽ በመሆናቸው፤ በቀጥታ ጨዋታውን ሊያዳሉ ይችላሉ ለማለት ባንችልም፤ የተዛባ ውሳኔ እንዳይሰጡ መጠንቀቅ እንዳለባቸው ይታመናል። ሆኖም አሁን ካለው የሁለቱ አገሮች ውጥረት አንጻር ዳኞቹ የሚሰጡት ውሳኔ ትንሽ የተዛባ ከሆነ ረብሻ እና ብጥብጥ እንዳይነሳ ስጋት አለ። በዚህም ምክንያት… የነገው ጨዋታ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል ብቻ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ እና በግብጽ መሃል የሚደረግ ሽኩቻ እንዳይሆን የብዙዎች ስጋት ነው።

በነገው ጨዋታ የቡድኑ አምበል ደጉ ደበበ በጉዳት ምክንያት ላይጫወት ይችላል፤ ተብሏል። ሌላው በአጥቂ ቦታ የሚጫወተው አዳነ ግርማም በተከታታይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት እስካሁን ሙሉ ጨዋታ ተጫውቶ አያውቅም። ነገም የሚገባው ከእረፍት በኋላ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ከምድቧ በ10 ነጥብ አንደኛ ሆና እየመራች ሲሆን፤ ከቡድኑ 1ኛ ሆና ካለፈች ወደሚቀጥለው ዙር ታልፋለች። በሚቀጥለውም ዙር ከየምድቡ ያሸነፉ አስር ቡድኖች ያሉበት ይሆናል። አስሩ አገሮች በሚወጣላቸው እጣ መሰረት፤ ከሚደርሳቸው አገር ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ አድርገው የሚያሸንፉት አምስት የአፍሪካ አገሮች በ2016፤ ብራዚል ውስጥ በሚደረገው የአለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋሉ።

የነገውን ጨዋታ ተከታትለን በኢ.ኤም.ኤፍ. Face book ገጻችን ላይ፤ ቀጥሎም በድረ ገጻችን ላይ የምናስተላልፍ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.