ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤

የተቀበሉትን የክህነት ኃላፊነት ጠብቀው በንጽሕና በመቆም እግዚአብሔርንና ሰውን ከማገልገል ይልቅ ሥጋዊ ጥቅምን አስቀድመው የተነሱ ጥቂት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና በምእመኑ መካከል ጸብና ጥላቻ ቀስቅሰው ሁከት እንዲሰፍን በማድረግ ባለፈው ሳምንት ለንደን ወደ ሚገኘው የኢህአዲግ መንግሥት ኤምባሲ በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን ያህል ነገር እንደ ግል ንብረት ለማስረከብ እንፈልጋለን በማለት  ከጠየቁ በኋላ ከዛ በማስከተል ቤተ ክርስቲያኗን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በመባል በኢህአዲግ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ለንደን ላይ ለተቋቋመው አካል አሳልፎ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደርና ንብረት ለማስረከብ በድርድር ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል። Save our churc from EPRDF Regime

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤

 1. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  March 25, 2013 at 8:04 AM

  111 +++ ተጠንቀቁ+++

  “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።”

  ኦሪት ዘጸአት ምዕ፥፳፫ ቁ፥፳፩

  222+++የእግዚአብሔርን ቤት በማንኣለብኝነት አትድፈር።
  እንደ ዖዛ ትቀሰፋለህና።

  “የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ።”
  ፪ኛ ሳሙኤል ምዕ፥፮ ቁ፥፯

  333+++የእግዚአብሔር ሰዎች ላይ በክፉ እጅህን አታንሳ።
  እጅህ እንደ ኢዮርብዓም ደርቃ ትቀራለችና።

  “ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የጮኸውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ኢዮርብዓም እጁን ከመሠዊያው አንሥቶ ያዙት አለ። በእርሱም ላይ የዘረጋት እጅ ደረቀች፥ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም።”
  መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕ፥፲፫ ቁ፥፬

  +++ኢዮርብዓምም ከዚያ በኋላ በአብያ ዘመን አልበረታም እግዚአብሔርም ቀሠፈው፥ ሞተም።
  መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕ፥፲፫ ቁ፥፳
  +++የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ፦

  ከእነዚህ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ምን አይነት ከስቲያናዊ ትምህርት እናገኛለን???መንፈሳዊ።በንጹህ ልቦናስ ራሳችን ብቻ መጀመሪያ ተቀራርበን ለመወያየት እንዳንችል ምን ይከለክለናል???ሰይጣን።ስለዚህ በፀሎት ለመጀመር ተጠራርተን እንገናኝ፤እንወያይ፤መፍትሄ እናገኛለን።
  እናም የእኔ ሃሳብ ይሄ ነው።
  ለመሆኑ የችግሩ ባለቤት ማን ነው???እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ተጠንቀቁ፤እኛ ኢትዮጵያቅያን የጉዳዩ ባለቤቶች ነን እንጂ።
  የችግሩ ባለቤት”ችግር ፈጣሪዎች”ናቸው፤እዚህ ላይ ነው መጠንቀቅ ያለብን።ችግር ፈጣሪዎች እነማን ናቸው??
  ሁለቱም ወገኖች ችግር ፈጣሪዎች አለመሆናቸውን ሊያሳምኑን ይሞክራሉ።አንደኛው ወገን አልፎም በሕዝብ መገናኛ ላይ ጩኸቴ ይሰማ ብለዋል፤በመሰረት የጮሁ ሁሉ ዕውነተኞች አይደሉም።ዕውነቱ ሁል ጊዜ የሚገኘው በሰላምና በፍቅር ቤት ብቻ ነው።በዚህ ትግል ውስጥ ብዙ ተዋንያን ይታያሉ።
  የዋሆችና ልበ ሩሩ አሉ፤ግርግር ፈጣሪዎች ይሹለከለካሉ፤ጥቅም ፈላጊዎች አሰፍስፈዋል፤አስመሳዮች በዝምታ ቤተክርስቲያናችን ስትሞትም ሆነ ስትታነቅ እንዳላዩ ይመላለሳሉ፤ግራ የገባቸው በተናጋሪዎች ተወናብደው”እግዚኦ እያሉ”ታምራት ይጠብቃሉ፤የሥልጣን ጥመኞች የዋልድባ ጥፋት አልበቃ ብሏቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር ባለቸው ተንኮል መሠረት ቅጥረኞችን አሰማርተው መነኩሴውን አባታችንን አባ ግርማ ከበደን ነጥለው ለመምታት ቀሳውስት ሰላዮችን በምዕመናን በኩል እየላኩ ምልጃ ይዘዋል።
  በዚህ መሃል እንደ አቶ ወንድሙ መኮንን ያሉ፣”የምንለው ይሰማ”የሚሉ የሐገር ተቆርቋሪ ሐቀኞች ቃላቸው እንዳይሰማ፣ማንነታቸውን ደብቀው ለሥጋዊ ጥቅም ከጎናቸው የሚርመሰመሱ እንዳሉ በሕሊና የማጉያ መንፅር መኖራቸውን አረጋግጫለሁ።ያም-ሆነ-ይህ መፍትሔው ምንድነው ለሚለው ተገቢውን ውሳኔ ለማግኘት ምን ይደረግ ነው።እኔም የምሰጠው ሃሳብ በአማራጭነት፦

  የኢትዮጵያ ኮምውኒቲ በለንደን፣በሦስተኛ ወገን ሁኖ ተቃዋሚውን እና ደጋፊውን እንዲያስታርቅ የባለቤትነት ሥልጣን በተለቀመ(ፔትሽን)ፊርማ ኃላፊነት እንስጠው፤እናም ችግራችን ባለቤት አገኘ ማለት ነው።ይህ የሁለቱም ወገን የችግራችን ባለቤት የሚሆነው የኮምውኒቲው አካል ሙሉ ሥልጣን ይዞ መፍትሔ ይኾነኛል የሚለውን ሁሉ ያደርጋል።በግል የሚደረግ ጥሪ ግን አያዋጣም።የነአቶ ወንድሙ መኮንን ሥጋትም ተገቢና መሆንም ያለበት ቢሆንም፣ጥሪው የየዋሆች የሚመስለው እኛ ቤተክርስቲያናችንን ልናስጠብቅ የምንፈልገው ያህል ሰይጣን እንቅልፍ አለመተኛቱን መዘንጋት ነው።እያለቀሱ የቤተክርስቲያን አባቶችን መሳደብ ከሃጢያት አያነፃምና እባካችሁ እንዋደድ፤እንፋቀር።
  ስለዚህ የኢትዮጵያ ኮምውኒቲ በስልክ በኢሜል በቴክስት ወዘተ ጥሪ ከተሰብሳቢዎች ማረጋገጫ ሲያገኝ ስብሰባ ይጥራና ሥራውን ይጀምር።

  ለዚህ መልካም ሥራ ላይ በፀሎታችን እንታገዝ።አንድዬ መለካሙን መንገድ ያሳየን።

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፤ቸሩ ፈጣሪያችንም ይጠብቅልን።

 2. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  March 25, 2013 at 12:03 PM