“ለምን እንደታሰርኩ አላውቀውም፡፡ ለምን እንደተፈታውሁም አላውቅም” ተመስገን

ጓዶች ተመልሰናል!!!
በድምሩ ለስድስት ቀናት ያህል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ነበርኩ፡፡ ለምን እንደታሰርኩ አላውቀውም፡፡ ለምን እንደተፈታውሁም አላውቅም፡፡ ዐቃቢ ህግ ግን‹‹ የዱርዬ ተግባር›› ፈፅሞብኛል፡፡ ምክንያቱም ማዕከላዊ ጣቢያ ተጠርቼ ቃል የሰጠሁት ሐምሌ 25 ሆኖ ሳለ ዐቃቢ ህግ ግን በ24 የታተመችውን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን ለችሎቱ ከፍ አድርጎ እያሳየ እንዲህ አለ ‹‹ተመስገን ለፖሊስ ቃል ከሰጠም በኋላ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ላይ አመፅ መቀስቀሱን አላቋረጠም››፤ ዳኛውም ጋዜጣውን ተቀበለና ርዕሱ…ን አንብቦ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው፡፡ …አቤት! እንዴት አይነት ውሸት ነው?
የዐቃቢ ህግ ዱርዬነት ቀጥሏል፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣን ጠቅሶ ደግም ‹‹የታገደው ጋዜጣ በሲዲ ስላለኝ እለቀዋለው ሲል ዝቶ ለጋዜጣው ቃለ መጠይቅ ስለሰጠ በዋስ ከተለቀቀ ዛቻውን ይፈፅማል፤ ስለዚህም ዋስትና አይሰጠው፡፡ በተጨማሪም ከሀገር ሊወጣ ይችላል ››አለ፡፡
ዳኛው ጥያቄ አቀረበ ‹‹የታለ አዲስ አድማስ ጋዜጣ?››
‹‹አሁን አልያዝነውም፤ ከሰአት ግን ማቅረብ እንችላለን›› አለና ዐቃቢ ህግ ማጭበርበሩን ቀጠለ፡፡ …አቤት! እንዴት አይነት ዱርዬነት ነው እየተካሄደ ያለው?
የሆነ ሆኖ መታሰሬን ተከትሎ ሀዘን የገባችሁ እና የቆጫችሁ ጓዶች፣ እናቶችና አባቶች እነሆ ተመልሻለሁና ለፀሎታችሁም ለትግላችሁም እግዜር ያክብርልኝ፡፡ እግዜር ይስጥልኝ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 29, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.