ለመሆኑ ኢሕአዴግ አለ እንዴ? ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በዚያኛው ሰሞን ስለብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከእግዚአብሔር መንገድ መራቅና ስለሕዝበ ክርስቲያን የመንፈስና የልብ መሸፈት አንዳንድ ነጥቦችን ተናግሬ ነበር፡፡ አንድ ሦስት ያህል የነጻው ሚዲያ ድረገጾች አስተናግደውታል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክልኝ፤ መንግሥተ ሰማይንም ያውርስልኝ፡፡ ሙከራየ ጥቂቶችን ከገቡበት አረንቋ እንዲወጡ – እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ – ለማሳሰብ እንጂ ሃይማኖተኝነትን ለመክሰስ ወይ ለመውቀስ አይደለም፡፡ ሃይማኖት የሌለው ሰው ልጓም እንደሌለው የጋማ ከብት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ እንደመኖሩ በዚያው መጠን ሃይማኖት አለኝ የሚልም ሰው ከለየለት ሃይማኖት የለሹ ሰው ባላነሰ ምናልባትም በከፋ ደረጃ አጥፊ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ይስተዋላልና ያን መረዳትና ሲቻልም ማስቀረት እንዲቻለን በዚህ ረገድ የሚታዩብንን ማኅበረሰብኣዊ ህፀፆች በግልጽ መመልከቱ እንደጥፋት ሊወሰድ አይገባም፡፡ በግልጽ የሚታይንና ጥፋት የሚመስልን ነገር የማጋለጥ መብት ደግሞ ከማንም በችሮታ ሊሰጥ ወይ ሊከለከል የማይችል ሰው በመሆን ብቻ ሊገኝ የሚችል ሥልጣን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ  የእረኛ ማጋጣ በጎችን ቀበሮ እንደሚያስበላ መጠቆምም ዋናው ዓላማየ ነው፡፡  …
Read full in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 31, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.