ሃለፊነታቸውን የዘነጉት ግድ የለሽ ምሁራን – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በቅርቡ ናኦም ቺሞስኪ: የኤም አይ ቲ (M.I.T.) ዩኒቨርሲቲ የስነ ቋንቋ ፕሮፌሰርና የአሜሪካ ቀደምት ምሁር፤ ለአልጀዚራ ስለአሜሪካ የቀለም ሰዎችና ምሁራን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ምሁሮቹ ሃላፊነት ጉድለትና ግድ የለሽነት አንደሚያሳዩ መግለጫ ሰጥተው ነበር:: ላለፉት 4 አሰርት ዓመታት የ84 ዓመቱ ቺሞስኪ ተጋፍጠው ፤ ሃይላነ ጉልበተኞች ነን የሚሉትንም በሃቅ አለንጋ ሲሸነቁጣቸው ነበር፡፡ በቅርቡም የፕሬዜዳንት ኦባማን ደካማ ጎን አስመልክቶ ትችቱን ሲያሰሙ ፤ ፕሬዜዳንቱ ‹‹የዓለም አቀፍ የግድያ ዘመቻ ለመፈጸም›› የድሮን (ሰው አልባ አሮፕላን )ጦርነት አካሂደዋል›› በብለወ ነበር:: በሃቅኝነታቸው ምክንያት ቺሞስኪ ‹‹ግራ ክንፈኛ›› ‹‹አክራሪ ፖለቲከኛ›› ከዚያም አልፎ ‹‹ኮሚኒስት›› በመባል ተኮንኗል፡፡ በርካታ ዋጋ ቢስ ቅጽል ስሞችም ተለጥፎባቸዋል፡፡ ያሻውን ቢባሉም ተናጋሪው የዕድሜ ባለጸጋ ከቆሙበት ዓላማ ዝንፍ ሳይሉ፤ ያነሱትን ነጥብ ሳይለቁ ሳይስቱ ተጠናክሮ እንደቀጠሉ ነው፡፡አሁንም ካታሊዝምን፤ ኒዎ ሊቤራሊዝምን፤ግሎባላይዜሽንን፤ጦር ሰባቂነትን፤ ሙስናን፤ ጭቆናን፤ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀምንና በስልጣን መባለግን፤የሰብአዊ መብት መደፈርን፤በአሜሪካና በሌሎችም ሃገሮች ያለውን ሁኔታ ይተቻሉ፡፡ ከዚያ ባሻገር ደሞ የስነ ቋንቋ ምሁራዊ ተግባራቸዉን ከማከናወን ዝንፍ አላሉም ፡፡

Click here to read full story

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 22, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.