ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013

በአለም ዙርያ ለሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች

ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ የተጠራ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ

በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013

በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠይቀዉ አንድ ጥያቄ ነዉ። ይህም የአንድነትና ተባብሮ የመስራት ጥያቄ ነዉ። ይህንንም ጥያቄ ህብረተሰቡ በተገኘዉ መድረክ ላይ ሁሉ ሳያሰልስ እያነሳዉ ይገኛል። ከዚህ አኳያ ለዚህ ህዝባዊ ጥያቄ ሁሉም በጉዳዩ ያገባኛል የሚሉ ወገኖች ሁሉ ጊዜ ሳይሰጡ በመገናኘትና በዚህ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ላይ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዉ ሊወያዩበትና ሊመክሩበት አልፎም መፍትሄ ማስቀመጥና ይህንኑም ለማስፈጸም በጋራ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤትም ከተነሳለት ህብረተሰቡን የማስተባበር አላማ በመነሳት ከተባባሪ አዘጋጅ አካላት ጋር በመሆን፤ ለህብረተሰቡ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቆራጥ ምላሽ ለማሰጠት፤ ያለዉን ስርአት በማስወገድ ሂደትና ስርአቱም ከተወገደ በሗላ ስለሚተካበት ሁኔታ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካሎች አማራጮቻቸውን የሚያቀርቡበት “ትግሉም የጋራ ድሉም የጋራ” በሚል መርህ ዙርያ ታላቅ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በጁላይ ወር 2013 (እኤአ) በዋሽንግተን ዲሲ ላይ እየተሰናዳ ይገኛል። ENTC july conference public 1st short announcement 03 22 13

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.