ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

የትግራይ ህዝብና ህወሓት! (በአብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

እውነት ነው። የህወሓት መሪዎች የትጥቅ ትግሉ ጀመሩት። ደርግ ዓማፅያኑ ለማጥፋትና ትግራይን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ መውሰድ ጀመረ። ትግራይ የጦርነት ኣውድማ ሆነች። የትግራይ ገበሬዎች በሰላም የእርሻ ስራቸው ማከናወን ኣቃታቸው። የደርግ ወታደሮች ገበሬዎቹን ማስፈራራት፣ ሴቶችን መድፈር፣ ወጣቶችን በግደል (በጥርጣሬ) ተያያዙት።

በደርግ ኣሰራር የተማረረው የትግራይ ገበሬ ጫካ ገባ። እዛው ጫካ ከህወሓቶች ጋር ተቀላቀለ። ኣብዛኛው ታጋይ (ገበሬ ወይ ኣርሶ ኣደር) ደርግን ለመታገል ጠመንጃ ያነሳው በደርግ ስርዓት በነበረ ጥሩ ያልሆነ የሰለማዊ ሰዎች ኣያያዝ እንጂ እንደሚነገረን እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ። በዚ ምክንያት በትግራይ ከኣንድ ቤተሰብ ቢያንስ ኣንድ ታጋይ (የተሰዋም በህይወት ያለም) ነበር (ኣለ)።
abraha desta
ነገር ግን ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም። ምሳሌዎችን ልጥቀስ።

ምሳሌ ኣንድ

የትግራይ ኣርሶ ኣደር የታገለበት ዓላማና የመሪዎቹ ለየቅል ነበር። በ1983 ዓም የህወሓት መሪዎች ኣራት ኪሎ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ የመሪዎቹ ዓላማ ለታጋይ ገበሬዎቹ ግልፅ ሆነ። በታጋዮቹና መሪዎች የዓላማ ልዩነት ግልፅ ሆነ። ታጋይ ገበሬዎቹ ጥያቄ ኣስነሱ። ጥያቂያቸው ምን ነበር??? ስድስት ጥያቄዎች:

(1) የኤርትራ ረፈረንደም (ነፃነት ወይ ባርነት የሚል ኣማራጭ) ስሕተት ነው፤ ለሀገር ኣንድነት መስራት ሲጠበቅብን ምንሊክ የሰራው ስሕተት እየደገምን ነው (ኃይለስላሴ እንኳ ለማስተካከል ሞክሮ ነበር)።

(2) የባህር በር (ወደብ) ያስፈልገናል። ሁሉም ነገር ለሻዕቢያ መስጠትና ኣገልጋይ መሆን በታሪክ ተጠያቂዎች ያደርገናል።

(3) የተታገልንበት ዓላማ መንገዱ እየሳተ ነው። ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ኣልነበረም፤ ዲሞክራሲ ማስፈን ነው።

(4) ሙስና እየተስፋፋ ነው፣ ትግላችንና መስዋእትነቻን በኣሉታዊ መልኩ ይጎደዋል።

(5) የደርግ መሪዎች እንጂ ሁሉም የደርግ ወታደሮች ጠላቶቻችን ኣይደሉም፤ በመከላከያ ሰራዊታችን ይጠቃለሉ፣ ብዙ የሰለጠኑና የሀገር ሃብት ፈሰስ የተደረገባቸው ናቸው።

(6) ሻዕቢያ ሊወረን እየተዘጋጀ ነው፤ ወታደራዊ ዓቅሙ እየገነባ ነው። እኛ ደግሞ ሀገራዊ መከላከያ ሰራዊት ይኑረን።

የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ። ነገር ግን ጥያቄዎቹ ወድያው ሻዕቢያ ጀሮ ደረሱ። የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ ኣፈዎርቂ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተነጋገሩበት። እንደዉጤቱም በ1985 ዓም ከ32, 000 በላይ የሚሆኑ የህወሓት ታጋዮች (ጥያቄ ያነሱ) እንዲባረሩ ተደረገ።

እንኳን የትግራይ ህዝብ በሙሉ፣ ህወሓት የታጋዮቹ ድጋፍ የለውም። መረጃ ስለሌለን ግን ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣድርገን እናስባለን።

ምሳሌ ሁለት

ሑመራ ኣከባቢ ነው፣ ልዩ ስሙ ማይካድራ። ኣንድ የድሮ ታጋይ ሴት ሦስት ልጆች ብቻዋ ታሳድጋለች። የማይካድራ ህዝብ (እንደሌላው ሁሉ) በመለስ ሞት ምክንያት የሓዘን ሰልፍ እንዲያደርግ በካድሬዎች ታዘዋል። ሴትየዋ በሓዘን ሰልፉ ኣልተገኘችም። በፖሊስ ተይዛ እንድትታሰር ተደረገ (የታሰሩ ብዙ ናቸው ግን ይቺ ሴት መረጥኩኝ)። በፖሊስ ለምን እንዳልተገኘች ተጠየቀች።

ሴትየው: ስራ ስለበዛብኝ ነው ያልመጣሁት

ፖሊስ: ስራ ቢበዛብሽስ??? ስራ ከመለስ ይበልጣል?

ሴትየው: እኔ ኮ ብቻየን ሦስት ልጆች ኣሳድጋለሁ።
ፖሊስ: እና?

ሴትየው: እናማ ስራ ይበልጥብኛል። ደሞኮ ሞት ብርቅ ኣይደለም። መስዋእትነት ኮ እናውቀዋለን። ባሌን ታውቀዋለህ። ታጋይ ነበር። ድሮ ተሰውተዋል። ልጆቹ ማሳደግ ኣይችልም። የኔና የተሰዋው ባለቤቴ ሓላፊነት ተሸክሜ ልጆቻችን ለማሳደግ ሌት ተቀን መስራት ኣለብኝ። መለስ ከሞተ እናንተ ቅበሩት።

ፖሊስ: ኣንቺ ራስሽ ታጋይ ነበርሽ። ባልሽም ተሰውተዋል። መለስ ደግሞ የሰማእታት ኣርኣያ ነው። ስለዚ ልታዝኚለት ይገባል።

ሴትየው: መለስ ከምወደው ባሌ ኣይበልጥብኝም። ኣሳዛኝ መስዋእት ኮ ጫካ ዉስጥ ተሰውተው ያለቀባሪ ተጥለው የቀሩ፣ ሬሳቸው የጅብና ኣሞራ ሲሳይ የሆነ፣ (ኣብ ፈቀዶ ጎቦታትን ሽንጥሮታትን ዝተረፉ) እንጂ ……. መለስ ኮ ብዙ ነገር ኣይተዋል። ኣሁን ደግሞ በክብር፣ በስርዓት እያረፈ ነው። ባሌኮ የቀብር ስነስርዓት ኣልተደረገለትም። ምን ታካብዳላቹ?! በመለስ ሞት ግን ባሌና የትግል ጓደኞቼ (ስውኣት ብፆተይ) ኣስታውሼ ኣዝኛለሁ።

ሴትዮዋ ተፈታች። እኛ ግን የትግራይ ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ ይመስለናል። ዉስጡ እየነደደ ነው።

ምሳሌ ሦስት

በትግራይ ሓውዜን ኣከባቢ ነው። ኣንድ ኣብሮ ኣደጌ (ጓደኛየ) ኣስታወስኩ። ኣብረን እንማር ነበር (እስከ ስድስተኛ ክፍል)። ከስድስተኛ ክፍል በላይ ትምህርቱ መቀጠል ኣልቻለም። የልጁ ኣባት የህወሓት ታጋይ ነበር፤ ተሰውተዋል። ከኣያቶቹ ጋር ይኖራል። ኣያቶቹ ሦስት ልጆች ነበሯቸው። ሁሉም ተሰውተዋል። የቀራቸው የልጅ ልጃቸው (እሱ ብቻ) ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት ልጁ ከመንግስት የወሰደውን ብድር መመለስ ስላልቻለ ወደ ሑመራ ኣከባቢ ይጠፋል። ኣያቶቹ ይታሰራሉ። መታሰራቸው ሰምቶ መጣ። ብዙ ነገር ደረሰበት። የጣብያ (ቀበሌ) ካድሬዎቹ ተቃወማቸው። ካድሬዎቹ ኣስተዳዳሪዎችም ኣባቱ የተሰዋበት ዓላማ ተቃወመ ብለው የኣከባቢው ሰዎች ከነሱ ቤተሰብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ተነገራቸው። (ያ ሦስት ልጆች የተሰውበት ቤተሰብ እንዲገለል ተደረገ)። በኣሁኑ ሰዓት ግን ይሄን የማግለል ስትራተጂ እየተውት ይገኛሉ።

ምሳሌ ኣራት

በትግራይ ኣስተማሪዎች በገዢው ፓርቲ የሚደርሳቸው ኣስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ በደል በመቃወም የተለያዩ እርምጃዎች የሚወስዱበት ኣጋጣሚ ኣለ። ተደጋጋሚ የስራ ማቆም ኣድማ ይደረጋል። ኣንዳንዴም የመምህርነት ስራው ጠቅልሎ የመተው ነገር ኣለ። ለምሳሌ ትግራይ ምስራቃዊ ዞን የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሏል። ነጋሽ ኣከባቢ በሚገኝ ኣንድ ትምህርትቤት ሁሉንም ኣስተማሪዎች (ዳይሬክተሩ ጨምሮ) ትምህርትቤቱ ዘግተው ጠፍተዋል። ግን የሚዘግበው ሰው የለም።

ምሳሌ ኣምስት

በኣንዳንድ ኢትዮዽያውያን የትግራይ ተወላጆች የኢህኣዴግ መንግስት በመደገፍ ኢትዮዽያውያንን ይበድላሉ ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ብዙዎች ይህንን እንደሚቃወሙ እንዴት ልንገራቹ?

ዓረና ትግራይ ፓርቲ በሺዎች የሚቆጠሩ ኣባላት እንዳሉት ሰምቻለሁ። እነዚህ ታድያ ህወሓት የሚቃወሙ ኣይደሉምን? ዴምህት የተባለ ኣማፂ ቡድን 60 ሺ ወታደሮች እንዳሉት ይነገራል። 60 ሺው ትክክል ላይሆን ይችላል። ግን ከ 20-25 ሺ ወታደር እንደሚኖረው ግን ይገመታል። እንዚህ ሁሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው።

በ1997/98 ዓም ከሻዕቢያ ሬድዮ በሰማሁት መረጃ መሰረት (ቃለ መጠይቅ ሲደረግባቸው) ብዙዎቹ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ነበሩ። ወደ ኤርትራ የገቡበት ምክንያት ሲያስረዱ በ1997 ና98 በነበረ የህዝብ ዓመፅ የተወሰደ እርምጃ በመቃወም ነበር። ስለዚ ሁሉም የትግራይ ህዝብ ገዢው ስርዓት ይደግፋል ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው።

በሌላ በኩል ስናየው ደግሞ ስራ ነው። ኣንድ ሰው ስራ ፈልጎ ወደ ፖሊስነት ወይ ውትድርና ሊገባ ይችላል። የእንጀራ ጉዳይ ነው። ከገባ ታድያ (ደመወዙን ለማግኘት) የታዘዘውን መስራት ኣለበት። ካልሰራ ይባረራል፤ ከተባረረ መኖር ኣይችልም (ሌላ ስራ እስካላገኘ ድረስ)። ስለዚ ጠንክሮ ቢሰራ ኣይደንቀኝም።

ባጠቃላይ የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።

በመጨረሻም

እንደው ሁሉንም ትተን፣ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ቢደግፍ (ከህወሓት ጎን ቢቆም) ችግሩ ምንድነው? ኣንድ ህዝብ የፈለገውን የመደገፍ ወይ የመቃወም መብቱ የተጠበቀ ነው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን (በፍላጎቱ ኣይደግፍም እንጂ) ቢደገፍ ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱ ‘ለምን ህወሓትን ትደግፋለህ?’ ሊባል ኣይገባም። ሌሎች ህዝቦች ህወሓትን የመቃወም መብት ያላቸው ያህል የትግራይ ህዝብም የመደገፍ መብት ኣለው።

ስለዚ (1) ሁሉንም የትግራይ ህዝብ (ብዙዎች እንደሚያስቡት) የህወሓት ደጋፊ ኣለመሆኑ እንዲታወቅ። (2) የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ይደግፋል ብሎ መውቀስም ተገቢ ኣይደለም።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

11 Responses to ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

 1. አለም

  August 16, 2013 at 9:01 AM

  አብርሃ ደስታ። በሌላ አነጋገር ምን አገባችሁ? ነው የምትለው? የአገሪቱ ልማት በጣም ለተጎዱ ክልሎች ቅድሚያ አልሰጠም። በሁሉም ቅድሚያ ያገኘው መሪዎቹ የመጡበት ትግራይ ነው፤ ለምን? ሲባል። ትግራይስ ኢትዮጵያ አይደለም ወይ? አላችሁን። የትግራይ ተወላጆች በሁሉም ክልል ተዘዋውረው ሥራ መሥራት ንብረት ማፍራት ሲችሉ፤ ሌሎቹ ከክልላቸው እንዳይወጡ የተደረገው በደል ነው ሲባል። ትግራይ ኢትዮጵያዊ አይደለም ወይ? አላችሁ። በደል መሆኑን ላለመቀበል ምክንያት ትደረድራላችሁ። አንተም ተራህን እንደ ስዬ አብርሃ ሌላኛው ልብ አድርቅ ሆነሃል። ትግራይ አይልማ ያለ የለም። ሌላው ለምን እኩል አይታይም ነው ነገሩ። ለመሆኑ ፎቶህን እንዲህ ማተለቁ ምን ለማለት ነው?

  • tazabit

   August 17, 2013 at 12:59 PM

   wow Abraha, you are complaining because not all of the Tigray folks got a share of the cake ha? you’re jumping up and down because TPLF threw a cookie at some of you ‘Tagays’ instead?….just so you know the rest of none-tigray ethnic people of Ethiopia don’t even have food to eat.So stop this nonsense of ‘please feel sorry for Tigray people’ jargon!!

  • Andnet Lehager

   August 20, 2013 at 2:30 PM

   ሁሉም የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ያለመሆኑን፡ ከግለሰብ አንስቶ፡ ለምን አይደለንም ብሎ የሚነሳ ቡድን አልሰማንም፤ አላየንም ከውዱ እውነታኛ ሃቀኛው ክቡር አቶ ገበረመድህን አርአያ በስተቀር። በተለይ በውጪ ሃገር፡ አንድም ወያኔ ያልሆነ ትግሬ የለም። ከምሁር አንስቶ እስከ መሃይሙ፡ ገና እንገዛችኋለን እንገርፋችኋለን አይደል እንዴ እያሉ የሚተብቱት!!!!!!!!!!

 2. weshet alewdem

  August 16, 2013 at 11:53 AM

  aberham desta,most of what you said above is a lie but you told us un your final paragrafe that what if all the tigrean are on support of weyane.the problem of supporting weyane is weyane is a killer,weyane is the one who steal billions of dollar from ethiopia,weyane is divider,and weyane is not ethiopian that is the problem of supporting weyane.

 3. Mogos

  August 16, 2013 at 12:20 PM

  Dear writer, TPLF destroyed the country Ethiopia as whole.
  Many citizen of the country killed, torched,disappeared etc…..
  to support such a terrorist organisation(TPLF) is not business as usual.
  if some one in Germany support the nazis or Moculini in Italy or
  Stalin in Russia or Osama Biladen Saudi is this some thing as normal?…
  I don’t think so.
  Please don’t forget how many people were killed by this barbaric organisation.
  To support TPLF is not some thing as simple.

 4. Tola

  August 16, 2013 at 2:37 PM

  I like the point you stated on your conclusion. TPLF has not only damaged our political outlook but also it has poisoned the way we live our everyday lives. We have long way to go in the course of creating sustainable peace in the empire.
  Excellent analysis!

 5. Kolegnaw

  August 16, 2013 at 5:56 PM

  Mr Abraha..
  Unfortunatly,you can not substantiate your claim in action,the fact of the matter is,majority of Tigray people supports their fascist leaders.that is what the entire world is witnessing.when does the Tigray people say enough is enough when those evil woyanes are trying to wipe our Amara people from the face of the earth committing every king of atrocities including sterilizing Amara women.we will never forget that and there is a high price to be payed for that on Woyane side. It is a matter of time.

 6. Kolegnaw

  August 16, 2013 at 6:01 PM

  Mr Abraha..
  Unfortunatly,you can not substantiate your claim in action,the fact of the matter is,majority of Tigray people supports their fascist leaders.that is what the entire world is witnessing.when does the Tigray people say enough is enough when those evil woyanes are trying to wipe out Amara people from the face of the earth committing every kind of atrocities including sterilizing Amara women.we will never forget that and there is a high price to be payed for that on Woyane side. It is a matter of time.

 7. andnet berhane

  August 17, 2013 at 12:40 AM

  የትግራይ ህዝብ አልተጨቆነም የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ የበዛው ሕዝብ በርሱላ የሚደርሱ በደልና ግፍ እንድሚደርሰው ይገነዘባል ነገርግን እሚበዛው ጊዜ የምትሰጣቸው የነበሩ ግምገማዎች አውንታዊና በበቂ የሚያሳምኑ ነበሩ ነገርግን ደጋፊም ቢሆን ምን አለበት ? ለሚለው አጠር ያለ መልስ በምፍራቱ ደጋፊ መስሎ ይታያል ያም ከፍርሃትና ከሌለላው ሕዝቡ ጋር እንድይገናኝ ሆን ተብሎ በቁጥጥር እንድዋለና በፍርሃት እንድተሸበበ የታወቀ ነው ነገርግን ህዝ መብቱና እሱነቱ ሲረገጥ አቀርቅሮ መሳለፉ ያም ያጠራጥራል ስለዚህም በተቻለ መጠን መጭውን ማስተዋል ያስፈልጋል አንድ ትዝ ያለኝ በመቀለ ከተማ የሰማሁት አንድ ትዝታ በወቅቱ ሻለቃ ፍስሃ ደስታ የለውጥ ኃዋርያ ሆነው መጥተው ፤ለህዝብ ንግግር ሲያደርጉ ያልዋት ታል ሕማቅ ትግራዋይሲ ልቡ ከምሃገሩ ብለው ነበር፡ በኔ ፍች ደክማም ቢሆን ካለው ሰራአት አይላቀቅም እንድማለት ይመስለኛል አህንም አብረሃ ደስታ የሰጠኸው ካዛ የተለየ አይደልም ቢሆን ሰዓቱ ባደረገው በደልና ሶቆቃ የትግራይ ሕዝብ ጌጋ ካላለ ያስጠይቀዋል ይችግሩም ሰላባነው ነገርግን የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአብሮነት ለመኖን ታሪክ ያስተሳሰረዋል ይቅርታንም ያደርጋም ቢታሰብበት ይመረጣል

  • Teddy

   August 18, 2013 at 9:13 PM

   Abrha desta shame on you !!! shame on you !!! All what u telling us is we can have our cakes and eat it.

 8. tazabit

  August 17, 2013 at 1:00 PM

  wow Abraha, you are complaining because not all of the Tigray folks got a share of the cake ha? you’re jumping up and down because TPLF threw a cookie at some of you ‘Tagays’ instead?….just so you know the rest of none-tigray ethnic people of Ethiopia don’t even have food to eat.So stop this nonsense of ‘please feel sorry for Tigray people’ jargon!!